ክፍል 5
ኢየሱስ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያከናወነው አገልግሎት
“ብዙዎች በእሱ አመኑ።”—ዮሐንስ 10:42
በዚህ ክፍል ውስጥ
ምዕራፍ 83
ግብዣ—አምላክ የሚጋብዘው እነማንን ነው?
ኢየሱስ በአንድ ፈሪሳዊ ቤት እየተመገበ እያለ ስለ አንድ ታላቅ የራት ግብዣ ምሳሌ ተናገረ። ለሁሉም የአምላክ ሕዝቦች የሚሆን ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቷል። ትምህርቱ ምንድን ነው?
ምዕራፍ 84
ደቀ መዝሙር መሆን ምን ያህል ከባድ ኃላፊነት ነው?
የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ከባድ ኃላፊነት ነው። ኢየሱስ፣ የእሱ ደቀ መዝሙር መሆን ምን እንደሚጠይቅ በግልጽ ተናግሯል። ተከታዮቹ ሊሆኑ ያሰቡ አንዳንዶች በተናገረው ነገር ደንግጠው ይሆናል።
ምዕራፍ 85
ንስሐ በሚገባ ኃጢአተኛ መደሰት
ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ ኢየሱስ ከተራው ሰው ጋር በመቀራረቡ ተቹት። ኢየሱስም አምላክ ኃጢአተኞችን እንዴት እንደሚመለከታቸው ለማሳየት ምሳሌዎች ተናገረ።
ምዕራፍ 91
አልዓዛር ከሞት ተነሳ
ከአልዓዛር ትንሣኤ ጋር የተያያዙ ሁለት ቁልፍ ነገሮች የኢየሱስ ተቃዋሚዎች እንኳ ይህን ተአምር መካድ እንዳይችሉ አድርገዋል።
ምዕራፍ 96
ኢየሱስ ለአንድ ሀብታም አለቃ መልስ ሰጠ
ኢየሱስ፣ ሀብታም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ እንደሚቀል የተናገረው ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 98
ሐዋርያት ትልቅ ቦታ እንደሚፈልጉ እንደገና አሳዩ
ያዕቆብና ዮሐንስ በመንግሥቱ ለየት ያለ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፤ እንዲህ ዓይነት ፍላጎት ያላቸው ግን እነሱ ብቻ አይደሉም።
ምዕራፍ 99
ኢየሱስ ዓይነ ስውሮችን ፈወሰ እንዲሁም ዘኬዎስን ረዳው
ኢየሱስ በኢያሪኮ አቅራቢያ አንድን ዓይነ ስውር ከመፈወሱ ጋር በተያያዘ እርስ በርሱ የሚጋጭ የሚመስለው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንደማይጋጭ እንዴት ማወቅ እንችላለን?
ምዕራፍ 100
ስለ አሥሩ ምናን የተናገረው ምሳሌ
ኢየሱስ “ላለው ሁሉ ተጨማሪ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ሰው ላይ ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል” ሲል ምን ማለቱ ነው?