በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 ክፍል 6

የኢየሱስ የመጨረሻ አገልግሎት

‘እነሆ ንጉሥሽ ይመጣል።’—ማቴዎስ 21:5

የኢየሱስ የመጨረሻ አገልግሎት

በዚህ ክፍል ውስጥ . . .

ምዕራፍ 101

በቢታንያ በስምዖን ቤት የተደረገ ግብዣ

የአልዓዛር እህት የሆነችው ማርያም ያደረገችው ነገር ክርክር አስነሳ፤ ኢየሱስ ግን ደገፋት።

ምዕራፍ 102

ንጉሡ በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ

አምስት መቶ ዓመት ያስቆጠረ ትንቢት እንዲፈጸም አደረገ።

ምዕራፍ 103

ቤተ መቅደሱ እንደገና ጸዳ

በኢየሩሳሌም ያሉት ነጋዴዎች የሚያከናውኑት ሥራ ሕጋዊ ይመስላል፤ ታዲያ ኢየሱስ ዘራፊዎች ብሎ የጠራቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 104

አይሁዳውያን የአምላክን ድምፅ ሰምተው ያምኑ ይሆን?

በኢየሱስ በማመንና ይህን እምነት በተግባር በማሳየት መካከል ልዩነት አለ?

ምዕራፍ 105

በበለስ ዛፍ ተጠቅሞ ስለ እምነት ማስተማር

ኢየሱስ፣ እምነት ምን ያህል ኃይል እንዳለው ለደቀ መዛሙርቱ አስተማራቸው፤ እንዲሁም አምላክ የእስራኤልን ብሔር የሚተወው ለምን እንደሆነ ገለጸ።

ምዕራፍ 106

ስለ ወይን እርሻ የተነገሩ ሁለት ምሳሌዎች

ልጆቹ በወይን እርሻው ላይ እንዲሠሩ የጠየቃቸው አባት ምሳሌ ምን ትርጉም አለው? የወይን እርሻውን ክፉ ለሆኑ ገበሬዎች ያከራየው ሰው ምሳሌስ?

ምዕራፍ 107

ንጉሡ ታዳሚዎችን ወደ ሠርግ ድግስ ጠራ

ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ ትንቢት ነው።

ምዕራፍ 108

ኢየሱስን ለማጥመድ የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ

መጀመሪያ ፈሪሳውያንን፣ ከዚያም ሰዱቃውያንን በመጨረሻም ግንባር ፈጥረው የመጡ ተቃዋሚዎቹን ጸጥ አሰኘ

ምዕራፍ 109

ተቃዋሚዎቹን አወገዘ

ኢየሱስ ከእሱ የተለየ አመለካከት ያላቸውን የሃይማኖት መሪዎች ያልታገሣቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 110

ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ያሳለፈው የመጨረሻ ቀን

ድሃዋን መበለት እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ግሩም ትምህርት አስተማረ።

ምዕራፍ 111

ሐዋርያቱ ምልክት እንዲሰጣቸው ኢየሱስን ጠየቁት

ኢየሱስ የተናገረው ትንቢት በአንደኛው መቶ ዘመን የመጀመሪያ ፍጻሜውን አግኝቷል። ከዚያ በኋላስ የላቀ ፍጻሜ ይኖረው ይሆን?

ምዕራፍ 112

ንቁ ስለ መሆን የተሰጠ ትምህርት—ደናግሉ

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ግማሾቹ ሞኞች፣ ግማሾቹ ግን ልባሞች እንደሚሆኑ ማስተማሩ ነው?

ምዕራፍ 113

ትጉ ስለ መሆን የተሰጠ ትምህርት—ታላንቱ

ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ “ላለው ሁሉ ይጨመርለታል” የሚለውን ሐሳብ ያብራራል።

ምዕራፍ 114

ክርስቶስ በመንግሥቱ በበጎችና በፍየሎች ላይ ይፈርዳል

ኢየሱስ አስገራሚ ምሳሌ በመጠቀም፣ ዘላለማዊ ለሆነ ፍርድ መሠረት የሚሆነው ምን እንደሆነ ገለጸ።

ምዕራፍ 115

ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

የሃይማኖት መሪዎቹ፣ ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ቢሰጣቸው 30 የብር ሳንቲሞች ለመክፈል መስማማታቸው ምን ትርጉም አለው?

ምዕራፍ 116

በመጨረሻው ፋሲካ ላይ ትሕትናን ማስተማር

ባሪያ የሚያከናውነውን ሥራ በመሥራት ሐዋርያቱን አስገረማቸው።

ምዕራፍ 117

የጌታ ራት

ኢየሱስ ተከታዮቹ በየዓመቱ ኒሳን 14 ላይ የሚያከብሩት የመታሰቢያ በዓል አቋቋመ።

ምዕራፍ 118

ታላቅ መሆንን በተመለከተ ክርክር ተነሳ

ኢየሱስ በዚያው ምሽት ያስተማራቸውን ትምህርት ሐዋርያቱ ዘንግተውታል።

ምዕራፍ 119

ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት

ኢየሱስ ወደ አምላክ መቅረብ የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ ትልቅ ሐቅ አስተማረ።

ምዕራፍ 120

ፍሬ የሚያፈራ ቅርንጫፍና የኢየሱስ ወዳጅ መሆን

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ‘ፍሬ የሚያፈሩት’ እንዴት ነው?

ምዕራፍ 121

“አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ”

ዓለም ኢየሱስን ከገደለው ኢየሱስ ዓለምን አሸንፎታል የሚባለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 122

ኢየሱስ ያቀረበው የመደምደሚያ ጸሎት

ኢየሱስ፣ ከሰው ልጆች መዳን ይበልጥ አስፈላጊ ነገር እንዳከናወነ ግልጽ አደረገ።

ምዕራፍ 123

እጅግ አዝኖ እያለ ያቀረበው ጸሎት

ኢየሱስ “ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ” ብሎ የጸለየው ለምንድን ነው? ቤዛ ሆኖ እንዲሞት የተሰጠውን ሚና መወጣት እንደማይችል መግለጹ ይሆን?

ምዕራፍ 124

ክርስቶስ አልፎ ተሰጠ እንዲሁም ተያዘ

ይሁዳ በእኩለ ሌሊትም እንኳ ኢየሱስን ማግኘት ችሏል።

ምዕራፍ 125

ኢየሱስ ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ

የኢየሱስ የቀረበበት ሸንጎ ያሳለፈ ውሳኔ ፍርደ ገምድል ነው።

ምዕራፍ 126

ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው

የእምነት ሰው የሆነውና ኢየሱስን በጣም የሚወደው ጴጥሮስ እንዲህ በፍጥነት ለጌታው ጀርባውን ሊሰጠው የቻለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 127

ሳንሄድሪን ፊት ቀረበ፤ ከዚያም ወደ ጲላጦስ ተወሰደ

የሃይማኖት መሪዎቹ እውነተኛ ፍላጎት ተጋለጠ።

ምዕራፍ 128

ጲላጦስም ሆነ ሄሮድስ ምንም ጥፋት አላገኙበትም

ጲላጦስ፣ ኢየሱስን ለፍርድ ወደ ሄሮድስ የላከው ለምንድን ነው? ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ የመፍረድ ሥልጣን የለውም?

ምዕራፍ 129

ጲላጦስ “እነሆ፣ ሰውየው!” አለ

ጲላጦስ እንኳ ኢየሱስ አስደናቂ ባሕርያት እንዳሉት ተገንዝቧል።

ምዕራፍ 130

ኢየሱስ አልፎ ተሰጠ፤ ከዚያም ሊገደል ተወሰደ

ኢየሱስ የሚያለቅሱትን ሴቶች ለእሱ ሳይሆን ለራሳቸውና ለልጆቻቸው እንዲያለቅሱ የነገራቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 131

ምንም ጥፋት የሌለበት ንጉሥ በእንጨት ላይ ተሰቀለ

ኢየሱስ አብረውት ከተሰቀሉት ወንጀለኞች ለአንዱ ትልቅ ትርጉም ያለው ተስፋ ሰጠው።

ምዕራፍ 132

“ይህ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር”

በቀን የተከሰተው ተአምራዊ ጨለማ፣ የምድር መናወጡ እንዲሁም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ መቀደድ ወደ አንድ መደምደሚያ ያደርሳሉ።

ምዕራፍ 133

የኢየሱስ አስከሬን ተዘጋጅቶ ተቀበረ

ኢየሱስን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ለመቅበር የተጣደፉት ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 134

ባዶ መቃብር—ኢየሱስ ሕያው ሆነ!

ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ መጀመሪያ የተገለጠው ለሐዋርያቱ ሳይሆን ለሴት ደቀ መዛሙርቱ ነው።

ምዕራፍ 135

ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ለብዙዎች ተገለጠ

ኢየሱስ ከሞት መነሳቱን ለደቀ መዛሙርቱ ያረጋገጠላቸው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 136

በገሊላ ባሕር ዳርቻ

ጴጥሮስ ለኢየሱስ ያለውን ፍቅር ማሳየት የሚችልበት መንገድ ሦስት ጊዜ ተነገረው።

ምዕራፍ 137

ከጴንጤቆስጤ በፊት በርካቶች አዩት

ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱ ምን እንደሚቀበሉና እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ከሞት ከተነሳ በኋላ ሆኖም ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ደጋግሞ ተናገረ።

ምዕራፍ 138

ክርስቶስ በአምላክ ቀኝ

ኢየሱስ በጠላቶቹ ላይ እርምጃ የሚወስድበትን ጊዜ በሚጠባበቅበት ጊዜ ምን ያደርጋል?

ምዕራፍ 139

ኢየሱስ ምድርን ገነት ያደርጋል፤ ተልእኮውንም ይፈጽማል

መንግሥቱን ለአምላኩና ለአባቱ ከመስጠቱ በፊት የሚያከናውነው ብዙ ነገር አለ።