ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ የተከናወኑ ነገሮችን በሙሉ በዚህ መጽሐፍ ላይ ማንበብ ይቻላል።

መግቢያ

መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት

በወንጌሎች ላይ የሰፈሩት ስለ ኢየሱስ ትምህርቶችና ስላደረጋቸው ነገሮች የሚገልጹ ዘገባዎች በሕይወትህ ላይ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ።

ምዕራፍ 1

ከአምላክ የተላኩ ሁለት መልእክቶች

መልአኩ ገብርኤል ለማመን የሚከብዱ መልእክቶችን ተናገረ።

ምዕራፍ 2

ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ክብር ተሰጥቶታል

ኤልሳቤጥና በሆዷ የነበረው ፅንስ ኢየሱስን ያከበሩት እንዴት ነው?

ምዕራፉ 3

መንገድ የሚያዘጋጅ ሰው ተወለደ

ዘካርያስ የመናገር ችሎታው በተአምራዊ መንገድ ሲመለስለት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ትንቢት ተናገረ።

ምዕራፍ 4

ማርያም ሳታገባ ፀነሰች

ማርያም ያረገዘችው ከሌላ ወንድ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መሆኑን ስትነግረው ዮሴፍ አመናት?

ምዕራፍ 5

ኢየሱስ ተወለደ—የትና መቼ?

ኢየሱስ በታኅሣሥ ወር እንዳልተወለደ እንዴት እናውቃለን?

ምዕራፍ 6

ተስፋ የተሰጠበት ልጅ

ዮሴፍና ማርያም ሕፃኑን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደሱ ሲያመጡት፣ በዕድሜ የገፉ ሁለት እስራኤላውያን ስለ እሱ ትንቢት ተናገሩ።

ምዕራፍ 7

ኮከብ ቆጣሪዎች ወደ ኢየሱስ መጡ

በምሥራቅ ያዩት ኮከብ መጀመሪያ ኢየሱስ ወዳለበት ቦታ ሳይሆን ነፍሰ ገዳይ የሆነው ንጉሥ ሄሮድስ ወዳለበት ቦታ የመራቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 8

ከጨካኝ ገዢ አመለጡ

ከመሲሑ ጋር የተያያዙ ሦስት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ኢየሱስ ልጅ ሳለ ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል።

ምዕራፍ 9

በናዝሬት አደገ

ኢየሱስ ስንት ወንድሞችና እህቶች አሉት?

ምዕራፍ 10

የኢየሱስ ቤተሰብ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ

ዮሴፍና ማርያም ኢየሱስን ማግኘት ባለመቻላቸው በጣም ተጨንቀዋል፤ ኢየሱስ ደግሞ የት እንደሚሆን ወዲያው ባለማወቃቸው ተገረመ።

ምዕራፍ 11

መጥምቁ ዮሐንስ መንገዱን አዘጋጀ

አንዳንድ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ እሱ ሲመጡ ዮሐንስ አወገዛቸው። ለምን?

ምዕራፍ 12

ኢየሱስ ተጠመቀ

ኢየሱስ ፈጽሞ ኃጢአት ባይኖርበትም የተጠመቀው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 13

ኢየሱስ ፈተናዎችን ከተቋቋመበት መንገድ መማር

ለኢየሱስ የቀረበለት ፈተና ስለ ዲያብሎስ ሁለት ቁልፍ እውነታዎችን ያስገነዝበናል።

ምዕራፍ 14

ደቀ መዛሙርት ማፍራት ጀመረ

የኢየሱስ ስድስት የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርት መሲሑን ማግኘታቸውን ያሳመናቸው ምንድን ነው?

ምዕራፍ 15

ኢየሱስ የፈጸመው የመጀመሪያ ተአምር

ኢየሱስ፣ መመሪያ የሚሰጠው በሰማይ ያለው አባቱ እንጂ እናቱ እንዳልሆነች ገለጸላት።

ምዕራፍ 16

ለእውነተኛው አምልኮ ቅንዓት አሳየ

የአምላክ ሕግ፣ ሕዝቡ ለመሥዋዕት የሚሆኑ እንስሳትን ኢየሩሳሌም እንዲገዙ ይፈቅድ ነበር፤ ታዲያ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ በነበሩት ነጋዴዎች የተናደደው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 17

ኒቆዲሞስን በምሽት አስተማረ

‘ዳግመኛ መወለድ’ ሲባል ምን ማለት ነው?

ምዕራፍ 18

ኢየሱስ እየጨመረ ዮሐንስ ግን እየቀነሰ ሄደ

መጥመቁ ዮሐንስ ባይቀናም ደቀ መዛሙርቱ ግን ቀንተው ነበር።

ምዕራፍ 19

አንዲት ሳምራዊት አስተማረ

ኢየሱስ ምናልባትም ለማንም ያልተናገረውን ነገር ነገራት።

ምዕራፍ 20

በቃና የፈጸመው ሁለተኛ ተአምር

ኢየሱስ የአንድን ባለሥልጣን ልጅ 26 ኪሎ ሜትር ገደማ ከሚሆን ርቀት ላይ ፈወሰው።

ምዕራፍ 21

በናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ

ኢየሱስ፣ ባደገበት ከተማ የነበሩት ሰዎች ሊገድሉት የሞከሩት ምን ስለተናገረ ነው?

ምዕራፍ 22

አራት ደቀ መዛሙርት ሰው አጥማጆች ሊሆኑ ነው

ዓሣ አጥማጆች የሆኑትን ደቀ መዛሙርቱን ለየት ያለ የማጥመድ ሥራ እንዲያከናውኑ ጠራቸው።

ምዕራፍ 23

ኢየሱስ በቅፍርናሆም ታላላቅ ሥራዎችን አከናወነ

ኢየሱስ አጋንንትን ሲያስወጣ የአምላክ ልጅ መሆኑን ለሰዎች እንዳይናገሩ ይከለክላቸው ነበር። ለምን?

ምዕራፍ 24

በገሊላ በስፋት ሰበከ

ሰዎች ፈውስ ለማግኘት ሲሉ ወደ ኢየሱስ መጡ፤ እሱ ግን አገልግሎቱ የላቀ ዓላማ እንዳለው ገለጸላቸው።

ምዕራፍ 25

በሥጋ ደዌ የተያዘን ሰው በርኅራኄ ፈወሰ

ኢየሱስ ያደረገው ቀላል የሚመስል ሆኖም ትልቅ ትርጉም ያለው ነገር ለሚፈውሳቸው ሰዎች ከልብ እንደሚያስብ ያሳያል።

ምዕራፍ 26

“ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል”

ኢየሱስ በኃጢአትና በበሽታ መካከል ምን ዝምድና እንዳለ አሳይቷል?

ምዕራፍ 27

ማቴዎስ ተጠራ

ኢየሱስ በኃጢአታቸው ከሚታወቁ ሰዎች ጋር የተመገበው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 28

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የማይጾሙት ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ስለ አቁማዳ ምሳሌ በመናገር መልስ ሰጥቷቸዋል።

ምዕራፍ 29

በሰንበት መልካም ሥራ መሥራት ይፈቀዳል?

ኢየሱስ ለ38 ዓመት ሕመምተኛ ሆኖ የኖረውን ሰው በመፈወሱ አይሁዳውያን ስደት ያደረሱበት ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 30

ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው

አይሁዳውያን ኢየሱስ ራሱን ከይሖዋ ጋር እኩል እንዳደረገ ቢሰማቸውም ኢየሱስ፣ አምላክ ከእሱ እንደሚበልጥ በግልጽ ተናግሯል።

ምዕራፍ 31

በሰንበት እሸት መቅጠፍ

ኢየሱስ “የሰንበት ጌታ” እንደሆነ የተናገረው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 32

በሰንበት የተፈቀደው ምንድን ነው?

በሌላ ጊዜ የማይስማሙት ሰዱቃውያን እና ፈሪሳውያን በአንድ ጉዳይ ላይ ግንባር ፈጠሩ።

ምዕራፍ 33

የኢሳይያስን ትንቢት መፈጸም

ኢየሱስ፣ የፈወሳቸውን ሰዎች ስለ ማንነቱ ወይም ስላደረጋቸው ነገሮች ለሌሎች እንዳይናገሩ ያዘዛቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 34

ኢየሱስ አሥራ ሁለት ሐዋርያት መረጠ

በሐዋርያ እና በደቀ መዝሙር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

ምዕራፍ 35

ታዋቂው የተራራ ስብከት

ኢየሱስ በሰጠው ንግግር ላይ ያሉት ቁልፍ ነጥቦች ማብራሪያ።

ምዕራፍ 36

አንድ መቶ አለቃ ትልቅ እምነት አሳየ

ይህ የጦር መኮንን ያደረገው ነገር ኢየሱስን አስገርሞታል፤ ምን ይሆን ያደረገው?

ምዕራፍ 37

ኢየሱስ የአንዲት መበለትን ልጅ ከሞት አስነሳ

ይህን ተአምር የተመለከቱት ሰዎች ድርጊቱ ምን ትርጉም እንዳለው ስለተገነዘቡ በጣም ተደነቁ።

ምዕራፍ 38

ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ጥያቄ አቀረበ

መሲሑ ኢየሱስ መሆኑን መጥምቁ ዮሐንስ የጠየቀው ለምንድን ነው? ተጠራጥሮ ነው?

ምዕራፍ 39

መልእክቱን ለማይቀበል ትውልድ ወዮለት

ኢየሱስ፣ በፍርድ ቀን የአገልግሎቱ ማዕከል ከሆነችው ከቅፍርናሆም ይልቅ ለሰዶም እንደሚቀልላት ተናግሯል።

ምዕራፍ 40

ይቅርታ ስለ ማግኘት የተሰጠ ትምህርት

ኢየሱስ፣ ምናልባት ዝሙት አዳሪ ለሆነችው ሴት ኃጢአቷ ይቅር እንደተባለ ሲነግራት የአምላክን ሕግ መጣስ ስህተት እንዳልሆነ መግለጹ ነው?

ምዕራፍ 41

ተአምራት የፈጸመው በማን ኃይል ነው?

የኢየሱስ ወንድሞች፣ አእምሮውን እንደሳተ ተሰምቷቸው ነበር።

ምዕራፍ 42

ኢየሱስ ፈሪሳውያንን ገሠጻቸው

‘የነቢዩ ዮናስ ምልክት’ ምንድን ነው?

ምዕራፍ 43

ስለ መንግሥቱ የተነገሩ ምሳሌዎች

ኢየሱስ የመንግሥተ ሰማያትን ገጽታዎች ለማብራራት ስምንት ምሳሌዎች ተናገረ።

ምዕራፍ 44

ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አሰኘው

ኢየሱስ ነፋሱንና ማዕበሉን ጸጥ በማሰኘት ወደፊት በመንግሥቱ ሥር ስለሚኖረው ሕይወት ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቷል።

ምዕራፍ 45

በአጋንንት ላይ ያለው ኃይል

በርካታ አጋንንት በአንድ ሰው ላይ ሊያድሩ ይችላሉ?

ምዕራፍ 46

የኢየሱስን ልብስ በመንካቷ ተፈወሰች

በዚህ ወቅት በተፈጸመው ልብ የሚነካ ሁኔታ ኢየሱስ ኃይሉንና ርኅራኄውን አሳይቷል።

ምዕራፍ 47

አንዲት ልጅ ከሞት ተነሳች!

ኢየሱስ፣ የሞተችው ልጅ ተኝታለች ሲል ሰዎቹ ሳቁበት። እነሱ የማያውቁት፣ እሱ ግን የሚያውቀው ምን ነገር አለ?

ምዕራፍ 48

ተአምራት ቢፈጽምም በናዝሬት እንኳ ተቀባይነት አላገኘም

የናዝሬት ሰዎች ኢየሱስን ያልተቀበሉት በትምህርቱ ወይም በፈጸማቸው ተአምራት የተነሳ ሳይሆን በሌላ ምክንያት ነው።

ምዕራፍ 49

በገሊላ መስበክና ሐዋርያቱን ማሠልጠን

‘መንግሥተ ሰማያት ቀርቧል’ ሲባል ምን ማለት ነው?

ምዕራፍ 50

ስደት ቢኖርም ለመስበክ መዘጋጀት

ኢየሱስ፣ ሞትን እንዳይፈሩ ለሐዋርያቱ የነገራቸው ቢሆንም ስደት ሲያጋጥማቸው እንዲሸሹ ያበረታታቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 51

በልደት ግብዣ ላይ የተፈጸመ ግድያ

የሰሎሜ ጭፈራ ሄሮድስን በጣም ስላስደሰተው የጠየቀችውን ማንኛውንም ነገር እንደሚሰጣት ቃል ገባላት። ያቀረበችው ጥያቄ ግን ዘግናኝ ነው፤ ምን ብላ ይሆን?

ምዕራፍ 52

በጥቂት ዳቦና ዓሣ ሺዎችን መመገብ

ኢየሱስ የፈጸመው ተአምር በጣም አስገራሚ በመሆኑ በአራቱም ወንጌሎች ላይ ሰፍሯል።

ምዕራፍ 53

የተፈጥሮ ኃይሎችን መቆጣጠር የሚችል ገዢ

ኢየሱስ በውኃ ላይ ሲራመድና ነፋሱን ጸጥ ሲያሰኝ ሐዋርያቱ ምን ትምህርት አገኙ?

ምዕራፍ 54

ኢየሱስ—“ሕይወት የሚያስገኘው ምግብ”

ሕዝቡ ወደ ኢየሱስ ለመምጣት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ኢየሱስ የወቀሳቸው ለምንድ ነው?

ምዕራፍ 55

የኢየሱስ ንግግር ብዙዎችን አስደነገጠ

ኢየሱስ የተናገረው ነገር በጣም የሚዘገንን በመሆኑ በርካታ ደቀ መዛሙርቱ ትተውት ሄዱ።

ምዕራፍ 56

ሰውን የሚያረክሰው ምንድን ነው?

ወደ አፉ የሚገባው ነው ወይስ ከአፉ የሚወጣው?

ምዕራፍ 57

ኢየሱስ አንዲትን ልጅና መስማት የተሳነውን ሰው ፈወሰ

ሴትየዋ፣ ኢየሱስ ሕዝቧን ከቡችሎች ጋር ሲያነጻጽራቸው ቅር ያልተሰኘችው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 58

ዳቦውን አበዛ፤ ስለ እርሾ አስጠነቀቀ

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፣ ኢየሱስ ስለ እርሾ ሲናገር ምን ማለቱ እንደሆነ በኋላ ላይ ገባቸው።

ምዕራፍ 59

የሰው ልጅ ማን ነው?

የመንግሥቱ ቁልፎች ምንድን ናቸው? የሚጠቀምባቸው ማን ነው? የሚጠቀምባቸውስ እንዴት ነው?

ምዕራፍ 60

በተአምራዊ ሁኔታ ተለወጠ—ክርስቶስ በክብሩ ታየ

ኢየሱስ በተአምራዊ ሁኔታ የተለወጠው እንዴት ነው? የራእዩ ትርጉምስ ምንድን ነው?

ምዕራፍ 61

ኢየሱስ ጋኔን የያዘውን ልጅ ፈወሰ

ጋኔን የያዘውን ልጅ መፈወስ ያልተቻለው በእምነት ማነስ ምክንያት እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። እምነት ያነሰው ማን ነው? ልጁ፣ አባቱ ወይስ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት?

ምዕራፍ 62

ስለ ትሕትና የተሰጠ ጠቃሚ ትምህርት

አዋቂ ወንዶች ከትናንሽ ልጆች ጠቃሚ ትምህርት አገኙ።

ምዕራፍ 63

ኢየሱስ ማሰናከልንና ኃጢአትን በተመለከተ ምክር ሰጠ

በወንድሞች መካከል ከባድ አለመግባባት ቢፈጠር ሊወሰዱ የሚገባቸውን ሦስት እርምጃዎች ገለጸ።

ምዕራፍ 64

ይቅር ባይ የመሆን አስፈላጊነት

ኢየሱስ፣ ይቅር ባይ ያልሆነውን ባሪያ ምሳሌ በመጠቀም አምላክ ሌሎችን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ መሆናችንን ምን ያህል አክብዶ እንደሚመለከተው ገልጿል።

ምዕራፍ 65

ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዝ የሰጠው ትምህርት

ኢየሱስ፣ አንድ ሰው የእሱ ተከታይ እንዳይሆን እንቅፋት ሊሆኑበት የሚችሉ አመለካከቶችን ከሦስት ሰዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ገልጿል።

ምዕራፍ 66

ለዳስ በዓል ኢየሩሳሌም ተገኘ

ኢየሱስን የሚያዳምጡት ሰዎች፣ ‘ጋኔን ይዞታል’ ብለው ያሰቡት ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 67

“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”

የአይሁድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አባላት በሙሉ ኢየሱስን ተቃወሙት፤ ይሁንና ከመካከላቸው አንዱ ኢየሱስን ደግፎ ተናገረ።

ምዕራፍ 68

“የዓለም ብርሃን”—የአምላክ ልጅ

ኢየሱስ “እውነትም ነፃ ያወጣችኋል” ብሏል። ነፃ የሚወጡት ከምንድን ነው?

ምዕራፍ 69

አባታቸው አብርሃም ነው ወይስ ዲያብሎስ?

ኢየሱስ፣ የአብርሃም ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በምን እንደሆነ እንዲሁም አባቱ ማን እንደሆነ ገለጸ።

ምዕራፍ 70

ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነን ሰው ፈወሰ

ደቀ መዛሙርቱ አንድ ሰው ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነው ለምን እንደሆነ ጠየቁ። ኃጢአት ፈጽሞ ነው? ወላጆቹስ ኃጢአት ሠርተው ነው? ኢየሱስ ሰውየውን ሲፈውሰው ሕዝቡ የተለያየ ስሜት አደረበት።

ምዕራፍ 71

ፈሪሳውያን ዓይነ ስውር የነበረውን ሰው በጥያቄ አፋጠጡት

ዓይነ ስውር የነበረው ሰው ያቀረበው የመከራከሪያ ነጥብ ፈሪሳውያኑን አስቆጣቸው። ወላጆቹ እንደፈሩትም ከምኩራብ አባረሩት።

ምዕራፍ 72

ኢየሱስ 70 ደቀ መዛሙርትን እንዲሰብኩ ላከ

በይሁዳ ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱን ስለ መንግሥቱ እንዲያውጁ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው። ደቀ መዛሙርቱ ለሰዎች የሚሰብኩት የት ነው? በምኩራቦች ወይስ በቤታቸው?

ምዕራፍ 73

አንድ ሳምራዊ እውነተኛ ባልንጀራ መሆኑን አሳየ

ኢየሱስ የደጉን ሳምራዊ ታሪክ ተጠቅሞ ግሩም ትምህርት የሰጠው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 74

ስለ እንግዳ ተቀባይነትና ስለ ጸሎት የተሰጠ ትምህርት

ኢየሱስ ማርያምና ማርታ ቤት ሄደ። እንግዳ ስለ ማስተናገድ ምን አስተማራቸው? ስለ ምን ጉዳይ መጸለይ እንዳለባቸው ደቀ መዛሙርቱን ያስተማራቸውስ እንዴት ነው?

ምዕራፍ 75

ኢየሱስ የደስታ ምንጭ ምን እንደሆነ ገለጸ

ኢየሱስ ስለ “አምላክ ጣት” እና የአምላክ መንግሥት የደረሰባቸው እንዴት እንደሆነ በመግለጽ ለተቺዎቹ መልስ ሰጣቸው። በተጨማሪም ሰዎች እውነተኛ ደስታ ማግኘት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ገለጸ።

ምዕራፍ 76

ከአንድ ፈሪሳዊ ጋር ተመገበ

ኢየሱስ የፈሪሳውያንንና የጸሐፍትን ሃይማኖታዊ ግብዝነት አወገዘ። በሕዝቡ ላይ ምን ዓይነት ከባድ ሸክም ጭነውባቸዋል?

ምዕራፍ 77

ኢየሱስ ሀብትን በተመለከተ ምክር ሰጠ

ኢየሱስ ትላልቅ ጎተራዎች ስለሠራ አንድ ሀብታም ሰው የሚገልጽ ምሳሌ ተናገረ። ሀብትን ማሳደድ ያለውን አደጋ በተመለከተ የትኛውን ምክር በድጋሚ ሰጠ?

ምዕራፍ 78

ታማኙ መጋቢ፣ ዝግጁ ሆነህ ጠብቅ!

ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱ መንፈሳዊ ደህንነት እንደሚያሳስበው አሳይቷል። መጋቢው መንፈሳዊ ደህንነታቸውን በመጠበቅ ረገድ ምን ድርሻ ይኖረዋል? ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ የተሰጠው ምክር በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 79

በቅርቡ ጥፋት የሚመጣው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ፣ አድማጮቹ የእሱን እርዳታ የማይቀበሉና ንስሐ የማይገቡ ከሆነ እንደሚጠፉ ተናገረ። ኢየሱስ በአምላክ ፊት ስላላቸው አቋም ሊያስተምራቸው የሚሞክረውን ጠቃሚ ትምህርት ይቀበሉ ይሆን?

ምዕራፍ 80

ጥሩው እረኛ እና የበጎች ጉረኖዎች

በአንድ እረኛና በበጎቹ መካከል ያለው ግንኙነት ኢየሱስ ስለ ደቀ መዛሙርቱ ያለውን ስሜት ጥሩ አድርጎ ይገልጸዋል። ደቀ መዛሙርቱ ትምህርቶቹን ተረድተው ይከተሉት ይሆን?

ምዕራፍ 81

ኢየሱስና አብ አንድ የሆኑት እንዴት ነው?

ከኢየሱስ ተቺዎች አንዳንዶቹ፣ ራሱን ከአምላክ ጋር እኩል አድርጓል በሚል ከሰሱት። ኢየሱስ ክሳቸው ሐሰት መሆኑን ግሩም አድርጎ ያስረዳው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 82

ኢየሱስ በፔሪያ ያከናወነው አገልግሎት

ኢየሱስ፣ መዳን ለማግኘት ምን እንደሚያስፈልግ ለአድማጮቹ አብራራ። ምክሩ በዚያ ዘመን ጠቃሚ ነበር። ዛሬስ?

ምዕራፍ 83

ግብዣ—አምላክ የሚጋብዘው እነማንን ነው?

ኢየሱስ በአንድ ፈሪሳዊ ቤት እየተመገበ እያለ ስለ አንድ ታላቅ የራት ግብዣ ምሳሌ ተናገረ። ለሁሉም የአምላክ ሕዝቦች የሚሆን ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቷል። ትምህርቱ ምንድን ነው?

ምዕራፍ 84

ደቀ መዝሙር መሆን ምን ያህል ከባድ ኃላፊነት ነው?

የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ከባድ ኃላፊነት ነው። ኢየሱስ፣ የእሱ ደቀ መዝሙር መሆን ምን እንደሚጠይቅ በግልጽ ተናግሯል። ተከታዮቹ ሊሆኑ ያሰቡ አንዳንዶች በተናገረው ነገር ደንግጠው ይሆናል።

ምዕራፍ 85

ንስሐ በሚገባ ኃጢአተኛ መደሰት

ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ ኢየሱስ ከተራው ሰው ጋር በመቀራረቡ ተቹት። ኢየሱስም አምላክ ኃጢአተኞችን እንዴት እንደሚመለከታቸው ለማሳየት ምሳሌዎች ተናገረ።

ምዕራፍ 86

ጠፍቶ የነበረው ልጅ ተመለሰ

ኢየሱስ ስለ አባካኙ ልጅ ከተናገረው ምሳሌ ምን እንማራለን?

ምዕራፍ 87

አርቆ በማሰብ ዕቅድ ማውጣት

ኢየሱስ፣ ተንኮለኛና ሙሰኛ የሆነን የቤት አስተዳዳሪ ምሳሌ በመጠቀም አንድ አስገራሚ ሐቅ አስተማረ።

ምዕራፍ 88

የሀብታሙ ሰውና የአልዓዛር ሁኔታ ተለወጠ

የኢየሱስን ምሳሌ ለመረዳት ቁልፉ፣ ሁለቱ ዋነኛ ገጸ ባሕርያት እነማንን እንደሚያመለክቱ ማወቅ ነው።

ምዕራፍ 89

ወደ ይሁዳ ሲጓዝ በፔሪያ አስተማረ

ኢየሱስ ደጋግመው የበደሉንንም እንኳ ይቅር ለማለት የሚረዳንን ባሕርይ ጎላ አድርጎ ገልጿል።

ምዕራፍ 90

“ትንሣኤና ሕይወት”

ኢየሱስ በእሱ ‘የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ እንደማይሞት’ ሲናገር ምን ማለቱ ነው?

ምዕራፍ 91

አልዓዛር ከሞት ተነሳ

ከአልዓዛር ትንሣኤ ጋር የተያያዙ ሁለት ቁልፍ ነገሮች የኢየሱስ ተቃዋሚዎች እንኳ ይህን ተአምር መካድ እንዳይችሉ አድርገዋል።

ምዕራፍ 92

የሥጋ ደዌ የነበረበት ሰው አመስጋኝነት አሳየ

የተፈወሰው ሰው ኢየሱስን ብቻ ሳይሆን አምላክንም አመስግኗል።

ምዕራፍ 93

የሰው ልጅ ይገለጣል

የክርስቶስ መገኘት ከመብረቅ ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 94

ሁለት አስፈላጊ ነገሮች—ጸሎትና ትሕትና

ኢየሱስ ስለ ክፉው ዳኛ እና ስለ አንዲት መበለት በተናገረው ምሳሌ ላይ አንድን ባሕርይ አጉልቷል።

ምዕራፍ 95

ስለ ፍቺና ልጆችን ስለ መውደድ የተሰጠ ትምህርት

ኢየሱስ ለትናንሽ ልጆች ያለው አመለካከት ከደቀ መዛሙርቱ በጣም የተለየ ነው። ለምን?

ምዕራፍ 96

ኢየሱስ ለአንድ ሀብታም አለቃ መልስ ሰጠ

ኢየሱስ፣ ሀብታም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ እንደሚቀል የተናገረው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 97

የወይኑ እርሻ ሠራተኞች ምሳሌ

ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች፣ ኋለኞች የሆኑ ደግሞ ፊተኞች የሚሆኑት እንዴት ነው?

ምዕራፍ 98

ሐዋርያት ትልቅ ቦታ እንደሚፈልጉ እንደገና አሳዩ

ያዕቆብና ዮሐንስ በመንግሥቱ ለየት ያለ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፤ እንዲህ ዓይነት ፍላጎት ያላቸው ግን እነሱ ብቻ አይደሉም።

ምዕራፍ 99

ኢየሱስ ዓይነ ስውሮችን ፈወሰ እንዲሁም ዘኬዎስን ረዳው

ኢየሱስ በኢያሪኮ አቅራቢያ አንድን ዓይነ ስውር ከመፈወሱ ጋር በተያያዘ እርስ በርሱ የሚጋጭ የሚመስለው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንደማይጋጭ እንዴት ማወቅ እንችላለን?

ምዕራፍ 100

ስለ አሥሩ ምናን የተናገረው ምሳሌ

ኢየሱስ “ላለው ሁሉ ተጨማሪ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ሰው ላይ ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል” ሲል ምን ማለቱ ነው?

ምዕራፍ 101

በቢታንያ በስምዖን ቤት የተደረገ ግብዣ

የአልዓዛር እህት የሆነችው ማርያም ያደረገችው ነገር ክርክር አስነሳ፤ ኢየሱስ ግን ደገፋት።

ምዕራፍ 102

ንጉሡ በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ

አምስት መቶ ዓመት ያስቆጠረ ትንቢት እንዲፈጸም አደረገ።

ምዕራፍ 103

ቤተ መቅደሱ እንደገና ጸዳ

በኢየሩሳሌም ያሉት ነጋዴዎች የሚያከናውኑት ሥራ ሕጋዊ ይመስላል፤ ታዲያ ኢየሱስ ዘራፊዎች ብሎ የጠራቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 104

አይሁዳውያን የአምላክን ድምፅ ሰምተው ያምኑ ይሆን?

በኢየሱስ በማመንና ይህን እምነት በተግባር በማሳየት መካከል ልዩነት አለ?

ምዕራፍ 105

በበለስ ዛፍ ተጠቅሞ ስለ እምነት ማስተማር

ኢየሱስ፣ እምነት ምን ያህል ኃይል እንዳለው ለደቀ መዛሙርቱ አስተማራቸው፤ እንዲሁም አምላክ የእስራኤልን ብሔር የሚተወው ለምን እንደሆነ ገለጸ።

ምዕራፍ 106

ስለ ወይን እርሻ የተነገሩ ሁለት ምሳሌዎች

ልጆቹ በወይን እርሻው ላይ እንዲሠሩ የጠየቃቸው አባት ምሳሌ ምን ትርጉም አለው? የወይን እርሻውን ክፉ ለሆኑ ገበሬዎች ያከራየው ሰው ምሳሌስ?

ምዕራፍ 107

ንጉሡ ታዳሚዎችን ወደ ሠርግ ድግስ ጠራ

ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ ትንቢት ነው።

ምዕራፍ 108

ኢየሱስን ለማጥመድ የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ

መጀመሪያ ፈሪሳውያንን፣ ከዚያም ሰዱቃውያንን በመጨረሻም ግንባር ፈጥረው የመጡ ተቃዋሚዎቹን ጸጥ አሰኘ

ምዕራፍ 109

ተቃዋሚዎቹን አወገዘ

ኢየሱስ ከእሱ የተለየ አመለካከት ያላቸውን የሃይማኖት መሪዎች ያልታገሣቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 110

ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ያሳለፈው የመጨረሻ ቀን

ድሃዋን መበለት እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ግሩም ትምህርት አስተማረ።

ምዕራፍ 111

ሐዋርያቱ ምልክት እንዲሰጣቸው ኢየሱስን ጠየቁት

ኢየሱስ የተናገረው ትንቢት በአንደኛው መቶ ዘመን የመጀመሪያ ፍጻሜውን አግኝቷል። ከዚያ በኋላስ የላቀ ፍጻሜ ይኖረው ይሆን?

ምዕራፍ 112

ንቁ ስለ መሆን የተሰጠ ትምህርት—ደናግሉ

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ግማሾቹ ሞኞች፣ ግማሾቹ ግን ልባሞች እንደሚሆኑ ማስተማሩ ነው?

ምዕራፍ 113

ትጉ ስለ መሆን የተሰጠ ትምህርት—ታላንቱ

ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ “ላለው ሁሉ ይጨመርለታል” የሚለውን ሐሳብ ያብራራል።

ምዕራፍ 114

ክርስቶስ በመንግሥቱ በበጎችና በፍየሎች ላይ ይፈርዳል

ኢየሱስ አስገራሚ ምሳሌ በመጠቀም፣ ዘላለማዊ ለሆነ ፍርድ መሠረት የሚሆነው ምን እንደሆነ ገለጸ።

ምዕራፍ 115

ኢየሱስ የሚያከብረው የመጨረሻ ፋሲካ ተቃረበ

የሃይማኖት መሪዎቹ፣ ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ቢሰጣቸው 30 የብር ሳንቲሞች ለመክፈል መስማማታቸው ምን ትርጉም አለው?

ምዕራፍ 116

በመጨረሻው ፋሲካ ላይ ትሕትናን ማስተማር

ባሪያ የሚያከናውነውን ሥራ በመሥራት ሐዋርያቱን አስገረማቸው።

ምዕራፍ 117

የጌታ ራት

ኢየሱስ ተከታዮቹ በየዓመቱ ኒሳን 14 ላይ የሚያከብሩት የመታሰቢያ በዓል አቋቋመ።

ምዕራፍ 118

ታላቅ መሆንን በተመለከተ ክርክር ተነሳ

ኢየሱስ በዚያው ምሽት ያስተማራቸውን ትምህርት ሐዋርያቱ ዘንግተውታል።

ምዕራፍ 119

ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት

ኢየሱስ ወደ አምላክ መቅረብ የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ ትልቅ ሐቅ አስተማረ።

ምዕራፍ 120

ፍሬ የሚያፈራ ቅርንጫፍና የኢየሱስ ወዳጅ መሆን

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ‘ፍሬ የሚያፈሩት’ እንዴት ነው?

ምዕራፍ 121

“አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ”

ዓለም ኢየሱስን ከገደለው ኢየሱስ ዓለምን አሸንፎታል የሚባለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 122

ኢየሱስ ያቀረበው የመደምደሚያ ጸሎት

ኢየሱስ፣ ከሰው ልጆች መዳን ይበልጥ አስፈላጊ ነገር እንዳከናወነ ግልጽ አደረገ።

ምዕራፍ 123

እጅግ አዝኖ እያለ ያቀረበው ጸሎት

ኢየሱስ “ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ” ብሎ የጸለየው ለምንድን ነው? ቤዛ ሆኖ እንዲሞት የተሰጠውን ሚና መወጣት እንደማይችል መግለጹ ይሆን?

ምዕራፍ 124

ክርስቶስ አልፎ ተሰጠ እንዲሁም ተያዘ

ይሁዳ በእኩለ ሌሊትም እንኳ ኢየሱስን ማግኘት ችሏል።

ምዕራፍ 125

ኢየሱስ ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ

የኢየሱስ የቀረበበት ሸንጎ ያሳለፈ ውሳኔ ፍርደ ገምድል ነው።

ምዕራፍ 126

ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው

የእምነት ሰው የሆነውና ኢየሱስን በጣም የሚወደው ጴጥሮስ እንዲህ በፍጥነት ለጌታው ጀርባውን ሊሰጠው የቻለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 127

ሳንሄድሪን ፊት ቀረበ፤ ከዚያም ወደ ጲላጦስ ተወሰደ

የሃይማኖት መሪዎቹ እውነተኛ ፍላጎት ተጋለጠ።

ምዕራፍ 128

ጲላጦስም ሆነ ሄሮድስ ምንም ጥፋት አላገኙበትም

ጲላጦስ፣ ኢየሱስን ለፍርድ ወደ ሄሮድስ የላከው ለምንድን ነው? ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ የመፍረድ ሥልጣን የለውም?

ምዕራፍ 129

ጲላጦስ “እነሆ፣ ሰውየው!” አለ

ጲላጦስ እንኳ ኢየሱስ አስደናቂ ባሕርያት እንዳሉት ተገንዝቧል።

ምዕራፍ 130

ኢየሱስ አልፎ ተሰጠ፤ ከዚያም ሊገደል ተወሰደ

ኢየሱስ የሚያለቅሱትን ሴቶች ለእሱ ሳይሆን ለራሳቸውና ለልጆቻቸው እንዲያለቅሱ የነገራቸው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 131

ምንም ጥፋት የሌለበት ንጉሥ በእንጨት ላይ ተሰቀለ

ኢየሱስ አብረውት ከተሰቀሉት ወንጀለኞች ለአንዱ ትልቅ ትርጉም ያለው ተስፋ ሰጠው።

ምዕራፍ 132

“ይህ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር”

በቀን የተከሰተው ተአምራዊ ጨለማ፣ የምድር መናወጡ እንዲሁም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ መቀደድ ወደ አንድ መደምደሚያ ያደርሳሉ።

ምዕራፍ 133

የኢየሱስ አስከሬን ተዘጋጅቶ ተቀበረ

ኢየሱስን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ለመቅበር የተጣደፉት ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 134

ባዶ መቃብር—ኢየሱስ ሕያው ሆነ!

ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ መጀመሪያ የተገለጠው ለሐዋርያቱ ሳይሆን ለሴት ደቀ መዛሙርቱ ነው።

ምዕራፍ 135

ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ለብዙዎች ተገለጠ

ኢየሱስ ከሞት መነሳቱን ለደቀ መዛሙርቱ ያረጋገጠላቸው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 136

በገሊላ ባሕር ዳርቻ

ጴጥሮስ ለኢየሱስ ያለውን ፍቅር ማሳየት የሚችልበት መንገድ ሦስት ጊዜ ተነገረው።

ምዕራፍ 137

ከጴንጤቆስጤ በፊት በርካቶች አዩት

ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱ ምን እንደሚቀበሉና እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ከሞት ከተነሳ በኋላ ሆኖም ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ደጋግሞ ተናገረ።

ምዕራፍ 138

ክርስቶስ በአምላክ ቀኝ

ኢየሱስ በጠላቶቹ ላይ እርምጃ የሚወስድበትን ጊዜ በሚጠባበቅበት ጊዜ ምን ያደርጋል?

ምዕራፍ 139

ኢየሱስ ምድርን ገነት ያደርጋል፤ ተልእኮውንም ይፈጽማል

መንግሥቱን ለአምላኩና ለአባቱ ከመስጠቱ በፊት የሚያከናውነው ብዙ ነገር አለ።

ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስችሉ ባሕርያት

በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ስምንት ባሕርያት ጎላ ብለው ታይተዋል።

የጥቅስ ማውጫ

በወንጌሎች ላይ የሚገኘው እያንዳንዱ ጥቅስ በዚህ መጽሐፍ ላይ የተብራራበትን ቦታ ለማግኘት ይህን ማውጫ ተጠቀም።

የምሳሌዎች ማውጫ

በዚህ መጽሐፍ ላይ እያንዳንዱ የኢየሱስ ምሳሌ የተብራራበትን ምዕራፍ ማግኘት ትችላለህ።

ስለ መሲሑ የተነገሩ አንዳንድ ትንቢቶች

በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ የተከናወኑትን ነገሮች፣ መሲሕ መሆኑን ከሚያረጋግጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችና እነዚህ ትንቢቶች በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተብራሩባቸው ምዕራፎች ጋር አዛምድ።

ኢየሱስ የኖረባቸውና ያስተማረባቸው ቦታዎች

ይህ ካርታ ኢየሱስ አገልግሎቱን ያከናወነባቸውን ቦታዎች ያሳያል።