በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 ክፍል 4

ኢየሱስ በይሁዳ ያከናወነው አገልግሎት

“የመከሩ ሥራ ኃላፊ ወደ መከሩ፣ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።”—ሉቃስ 10:2

ኢየሱስ በይሁዳ ያከናወነው አገልግሎት

በዚህ ክፍል ውስጥ . . .

ምዕራፍ 66

ለዳስ በዓል ኢየሩሳሌም ተገኘ

ኢየሱስን የሚያዳምጡት ሰዎች፣ ‘ጋኔን ይዞታል’ ብለው ያሰቡት ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 67

“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”

የአይሁድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አባላት በሙሉ ኢየሱስን ተቃወሙት፤ ይሁንና ከመካከላቸው አንዱ ኢየሱስን ደግፎ ተናገረ።

ምዕራፍ 68

“የዓለም ብርሃን”—የአምላክ ልጅ

ኢየሱስ “እውነትም ነፃ ያወጣችኋል” ብሏል። ነፃ የሚወጡት ከምንድን ነው?

ምዕራፍ 69

አባታቸው አብርሃም ነው ወይስ ዲያብሎስ?

ኢየሱስ፣ የአብርሃም ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በምን እንደሆነ እንዲሁም አባቱ ማን እንደሆነ ገለጸ።

ምዕራፍ 70

ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነን ሰው ፈወሰ

ደቀ መዛሙርቱ አንድ ሰው ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነው ለምን እንደሆነ ጠየቁ። ኃጢአት ፈጽሞ ነው? ወላጆቹስ ኃጢአት ሠርተው ነው? ኢየሱስ ሰውየውን ሲፈውሰው ሕዝቡ የተለያየ ስሜት አደረበት።

ምዕራፍ 71

ፈሪሳውያን ዓይነ ስውር የነበረውን ሰው በጥያቄ አፋጠጡት

ዓይነ ስውር የነበረው ሰው ያቀረበው የመከራከሪያ ነጥብ ፈሪሳውያኑን አስቆጣቸው። ወላጆቹ እንደፈሩትም ከምኩራብ አባረሩት።

ምዕራፍ 72

ኢየሱስ 70 ደቀ መዛሙርትን እንዲሰብኩ ላከ

በይሁዳ ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱን ስለ መንግሥቱ እንዲያውጁ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው። ደቀ መዛሙርቱ ለሰዎች የሚሰብኩት የት ነው? በምኩራቦች ወይስ በቤታቸው?

ምዕራፍ 73

አንድ ሳምራዊ እውነተኛ ባልንጀራ መሆኑን አሳየ

ኢየሱስ የደጉን ሳምራዊ ታሪክ ተጠቅሞ ግሩም ትምህርት የሰጠው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 74

ስለ እንግዳ ተቀባይነትና ስለ ጸሎት የተሰጠ ትምህርት

ኢየሱስ ማርያምና ማርታ ቤት ሄደ። እንግዳ ስለ ማስተናገድ ምን አስተማራቸው? ስለ ምን ጉዳይ መጸለይ እንዳለባቸው ደቀ መዛሙርቱን ያስተማራቸውስ እንዴት ነው?

ምዕራፍ 75

ኢየሱስ የደስታ ምንጭ ምን እንደሆነ ገለጸ

ኢየሱስ ስለ “አምላክ ጣት” እና የአምላክ መንግሥት የደረሰባቸው እንዴት እንደሆነ በመግለጽ ለተቺዎቹ መልስ ሰጣቸው። በተጨማሪም ሰዎች እውነተኛ ደስታ ማግኘት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ገለጸ።

ምዕራፍ 76

ከአንድ ፈሪሳዊ ጋር ተመገበ

ኢየሱስ የፈሪሳውያንንና የጸሐፍትን ሃይማኖታዊ ግብዝነት አወገዘ። በሕዝቡ ላይ ምን ዓይነት ከባድ ሸክም ጭነውባቸዋል?

ምዕራፍ 77

ኢየሱስ ሀብትን በተመለከተ ምክር ሰጠ

ኢየሱስ ትላልቅ ጎተራዎች ስለሠራ አንድ ሀብታም ሰው የሚገልጽ ምሳሌ ተናገረ። ሀብትን ማሳደድ ያለውን አደጋ በተመለከተ የትኛውን ምክር በድጋሚ ሰጠ?

ምዕራፍ 78

ታማኙ መጋቢ፣ ዝግጁ ሆነህ ጠብቅ!

ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱ መንፈሳዊ ደህንነት እንደሚያሳስበው አሳይቷል። መጋቢው መንፈሳዊ ደህንነታቸውን በመጠበቅ ረገድ ምን ድርሻ ይኖረዋል? ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ የተሰጠው ምክር በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 79

በቅርቡ ጥፋት የሚመጣው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ፣ አድማጮቹ የእሱን እርዳታ የማይቀበሉና ንስሐ የማይገቡ ከሆነ እንደሚጠፉ ተናገረ። ኢየሱስ በአምላክ ፊት ስላላቸው አቋም ሊያስተምራቸው የሚሞክረውን ጠቃሚ ትምህርት ይቀበሉ ይሆን?

ምዕራፍ 80

ጥሩው እረኛ እና የበጎች ጉረኖዎች

በአንድ እረኛና በበጎቹ መካከል ያለው ግንኙነት ኢየሱስ ስለ ደቀ መዛሙርቱ ያለውን ስሜት ጥሩ አድርጎ ይገልጸዋል። ደቀ መዛሙርቱ ትምህርቶቹን ተረድተው ይከተሉት ይሆን?

ምዕራፍ 81

ኢየሱስና አብ አንድ የሆኑት እንዴት ነው?

ከኢየሱስ ተቺዎች አንዳንዶቹ፣ ራሱን ከአምላክ ጋር እኩል አድርጓል በሚል ከሰሱት። ኢየሱስ ክሳቸው ሐሰት መሆኑን ግሩም አድርጎ ያስረዳው እንዴት ነው?