ዘፍጥረት 5:1-32

  • ከአዳም እስከ ኖኅ (1-32)

    • አዳም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ (4)

    • ሄኖክ ከአምላክ ጋር ሄደ (21-24)

5  የአዳምን ታሪክ የያዘው መጽሐፍ ይህ ነው። አምላክ አዳምን በፈጠረበት ቀን፣ በአምላክ አምሳል ሠራው።+  ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።+ በተፈጠሩበትም+ ቀን ባረካቸው፤ እንዲሁም ሰው* ብሎ ጠራቸው።  አዳም 130 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም እሱን የሚመስል ወንድ ልጅ በራሱ አምሳያ ወለደ፤ ስሙንም ሴት+ አለው።  አዳም ሴትን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።  ስለዚህ አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ።+  ሴት 105 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሄኖስን+ ወለደ።  ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።  ስለዚህ ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ።  ሄኖስ 90 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ቃይናንን ወለደ። 10  ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 11  ስለዚህ ሄኖስ በአጠቃላይ 905 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 12  ቃይናን 70 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም መላልኤልን+ ወለደ። 13  ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 14  ስለዚህ ቃይናን በአጠቃላይ 910 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 15  መላልኤል 65 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ያሬድን+ ወለደ። 16  መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ 830 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 17  ስለዚህ መላልኤል በአጠቃላይ 895 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 18  ያሬድ 162 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሄኖክን+ ወለደ። 19  ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 20  ስለዚህ ያሬድ በአጠቃላይ 962 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 21  ሄኖክ 65 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ማቱሳላን+ ወለደ። 22  ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ለ300 ዓመት ከእውነተኛው አምላክ* ጋር መሄዱን ቀጠለ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 23  ስለዚህ ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ። 24  ሄኖክ ከእውነተኛው አምላክ ጋር መሄዱን ቀጠለ።+ አምላክ ስለወሰደውም ከዚያ በኋላ አልተገኘም።+ 25  ማቱሳላ 187 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ላሜህን+ ወለደ። 26  ማቱሳላም ላሜህን ከወለደ በኋላ 782 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 27  ስለዚህ ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 28  ላሜህ 182 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ወንድ ልጅ ወለደ። 29  እሱም “ይህ ልጅ፣ ይሖዋ በረገማት ምድር+ የተነሳ ከምንለፋው ልፋትና ከምንደክመው ድካም በማሳረፍ ያጽናናናል”* በማለት ስሙን ኖኅ*+ ብሎ ጠራው። 30  ላሜህም ኖኅን ከወለደ በኋላ 595 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 31  ስለዚህ ላሜህ በአጠቃላይ 777 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 32  ኖኅ 500 ዓመት ከሆነው በኋላ ሴምን፣+ ካምንና+ ያፌትን+ ወለደ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “አዳም፤ የሰው ዘር።”
ቃል በቃል “ከአምላክ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “እፎይታ ያስገኝልናል።”
“እረፍት፤ ማጽናኛ” የሚል ትርጉም ሳይኖረው አይቀርም።