ምሳሌ 2:1-22

  • ጥበብ ያላት የላቀ ዋጋ (1-22)

    • ጥበብን እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቆ መሻት (4)

    • የማመዛዘን ችሎታ ይጠብቅሃል (11)

    • የሥነ ምግባር ብልግና ለውድቀት ይዳርጋል (16-19)

2  ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበልናትእዛዛቴን እንደ ውድ ሀብት ብታስቀምጥ፣+  2  ይህን ለማድረግ ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣+ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ልብህን ብታዘነብል፣+  3  ደግሞም ማስተዋልን ብትጣራና+ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ድምፅህን ብታሰማ፣+  4  እንደ ብር ተግተህ ብትፈልጋት፣+እንዲሁም እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣+  5  ያን ጊዜ ይሖዋን መፍራት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ፤+ደግሞም ስለ አምላክ እውቀት ትቀስማለህ።+  6  ይሖዋ ራሱ ጥበብ ይሰጣልና፤+ከአፉ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ይወጣል።  7  ለቅኖች ጥበብን* እንደ ውድ ሀብት ያከማቻል፤ንጹሕ አቋማቸውን* ጠብቀው ለሚመላለሱት ጋሻ ነው።+  8  የፍትሕን ጎዳና ይከታተላል፤የታማኞቹንም መንገድ ይጠብቃል።+  9  በዚህ ጊዜ ጽድቅ፣ ፍትሕና ትክክል የሆነውን ነገርይኸውም የጥሩነትን ጎዳና በሙሉ ትረዳለህ።+ 10  ጥበብ ወደ ልብህ ስትገባና+እውቀት ነፍስህን* ደስ ስታሰኝ፣+ 11  የማመዛዘን ችሎታ ምንጊዜም ይጠብቅሃል፤+ጥልቅ ግንዛቤም ይጋርድሃል፤ 12  ይህም አንተን ከክፉ መንገድ ለማዳንእንዲሁም ጠማማ ነገር ከሚናገር ሰው፣+ 13  በጨለማ መንገድ ለመጓዝቀናውን ጎዳና ከሚተዉ፣+ 14  መጥፎ ድርጊት በመፈጸም ሐሴት ከሚያደርጉ፣ጠማማ በሆኑ ክፉ ነገሮች ከሚደሰቱ፣ 15  መንገዳቸው ጠማማ ከሆነናአካሄዳቸው በተንኮል ከተሞላ ሰዎች አንተን ለመታደግ ነው። 16  ጋጠወጥ* ከሆነች ሴት፣ባለጌ* ሴት ከምትናገረው የሚያባብል* ቃል ያድንሃል፤+ 17  ይህች ሴት በወጣትነቷ የነበራትን የቅርብ ወዳጇን*+ የምትተውእንዲሁም ከአምላኳ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን የምትረሳ ናት፤ 18  ቤቷ ሰውን ይዞ ወደ ሞት ይወርዳልና፤አካሄዷም* በሞት ወደተረቱት ይወስዳል።+ 19  ከእሷ ጋር ግንኙነት ያላቸው* ሁሉ አይመለሱም፤የሕይወትንም መንገድ ዳግመኛ አያገኙም።+ 20  በመሆኑም የጥሩ ሰዎችን መንገድ ተከተል፤እንዲሁም ከጻድቃን ጎዳና አትውጣ፤+ 21  በምድር ላይ የሚኖሩት ቅኖች ብቻ ናቸውና፤በእሷም ላይ የሚቀሩት ነቀፋ የሌለባቸው* ናቸው።+ 22  ክፉዎች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፤+ከዳተኞችም ከእሷ ይወገዳሉ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ ወይም “ማስተዋል የታከለበት ጥበብን።”
^ እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል የሥነ ምግባር ንጽሕናን፣ ሁለት ልብ አለመሆንንና እንከን የለሽ መሆንን ያመለክታል።
^ ቃል በቃል “እንግዳ።” ከምትከተለው የሥነ ምግባር አቋም የተነሳ ከአምላክ ጋር የተቆራረጠችን ሴት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
^ ቃል በቃል “ባዕድ።” ከምትከተለው የሥነ ምግባር አቋም የተነሳ ከአምላክ የራቀችን ሴት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
^ ወይም “የሚያማልል።”
^ ወይም “ባሏን።”
^ ቃል በቃል “መንገዷም።”
^ ቃል በቃል “ወደ እሷ የሚገቡ።”
^ ወይም “ንጹሕ አቋማቸውን የሚጠብቁ።”