ምሳሌ 31:1-31

  • የንጉሥ ልሙኤል ቃል (1-31)

    • ባለሙያ ሚስትን ማን ሊያገኛት ይችላል? (10)

    • ታታሪና ትጉ ሠራተኛ ናት (17)

    • ‘የደግነት ሕግ በአንደበቷ አለ’ (26)

    • ልጆቿና ባሏ ያወድሷታል (28)

    • ውበትና ቁንጅና አላፊ ነው (30)

31  የንጉሥ ልሙኤል ቃል፤ እናቱ እሱን ለማስተማር የተናገረችው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘለ መልእክት፦+  2  ልጄ ሆይ፣ ምን ልበልህ?የማህፀኔ ልጅ ሆይ፣ ምን ልበልህ?የስእለቴ ልጅ ሆይ፣ ምን ልበልህ?+  3  ጉልበትህን ለሴቶች አትስጥ፤+ነገሥታትንም ለጥፋት የሚዳርግ መንገድ አትከተል።+  4  ልሙኤል ሆይ፣ ነገሥታት የወይን ጠጅ መጠጣት የለባቸውም፤አዎ፣ ነገሥታት ይህን ማድረግ አይገባቸውም፤ገዢዎችም “መጠጤ የት አለ?” ሊሉ አይገባም።+  5  አለዚያ ጠጥተው የተደነገገውን ሕግ ይረሳሉ፤የችግረኞችንም መብት ይጥሳሉ።  6  ሊጠፉ ለተቃረቡ ሰዎች መጠጥ፣+ከባድ ጭንቀት ለደረሰባቸውም* የወይን ጠጅ ስጧቸው።+  7  ጠጥተው ድህነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ዳግመኛ አያስታውሱ።  8  ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት አንተ ተናገርላቸው፤ሊጠፉ ለተቃረቡት ሰዎች ሁሉ መብት ተሟገት።+  9  ተናገር፤ በጽድቅም ፍረድ፤ለችግረኛውና ለድሃው መብት ጥብቅና ቁም።*+ א [አሌፍ] 10  ባለሙያ ሚስትን* ማን ሊያገኛት ይችላል?+ ዋጋዋ ከዛጎል* እጅግ ይበልጣል። ב [ቤት] 11  ባሏ ከልቡ ይታመንባታል፤አንዳችም ጠቃሚ ነገር አይጎድልበትም። ג [ጊሜል] 12  በሕይወቷ ዘመን ሁሉመልካም ነገር ታደርግለታለች እንጂ ክፉ ነገር አታደርግበትም። ד [ዳሌት] 13  ሱፍና በፍታ ታመጣለች፤በእጆቿ መሥራት ያስደስታታል።+ ה [ሄ] 14  እሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤+ምግቧን ከሩቅ ቦታ ታመጣለች። ו [ዋው] 15  ገና ሳይነጋም ትነሳለች፤ለቤተሰቦቿም ምግባቸውን፣ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች።+ ז [ዛየን] 16  በጥሞና ካሰበችበት በኋላ መሬት ትገዛለች፤በራሷ ጥረት* ወይን ትተክላለች። ח [ኼት] 17  ወገቧን ታጥቃ ለሥራ ትነሳለች፤*+ክንዶቿንም ታበረታለች። ט [ቴት] 18  ንግዷ ትርፋማ እንደሆነ ታስተውላለች፤መብራቷ በሌሊት አይጠፋም። י [ዮድ] 19  እጆቿ አመልማሎ የያዘ ዘንግ ይጨብጣሉ፤ጣቶቿም እንዝርት ይይዛሉ።*+ כ [ካፍ] 20  እጆቿን ለተቸገረ ሰው ትዘረጋለች፤ለድሃውም እጇን ትከፍታለች።+ ל [ላሜድ] 21  ቤተሰቦቿ ሁሉ የሚያሞቅ* ልብስ ስለሚለብሱበበረዶ ወቅት እንኳ አትሰጋም። מ [ሜም] 22  ለራሷ የአልጋ ልብስ ትሠራለች። ልብሷ ከበፍታና ከሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው። נ [ኑን] 23  ባሏ ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር በሚቀመጥበት በከተማዋ በሮች+በሰዎች ዘንድ በሰፊው የታወቀ ነው። ס [ሳሜኽ] 24  የበፍታ ልብሶች እየሠራች* ትሸጣለች፤ለነጋዴዎችም ቀበቶ ታስረክባለች። ע [አይን] 25  ብርታትንና ግርማን ትጎናጸፋለች፤የወደፊቱንም ጊዜ በልበ ሙሉነት ትጠባበቃለች።* פ [ፔ] 26  አፏን በጥበብ ትከፍታለች፤+የደግነት ሕግም* በአንደበቷ አለ። צ [ጻዴ] 27  የቤተሰቧን እንቅስቃሴ በደንብ ትከታተላለች፤የስንፍናንም ምግብ አትበላም።+ ק [ኮፍ] 28  ልጆቿ ተነስተው ደስተኛ ይሏታል፤ባሏ ተነስቶ ያወድሳታል። ר [ረሽ] 29  ባለሙያ* የሆኑ ብዙ ሴቶች አሉ፤አንቺ ግን፣ አዎ አንቺ ከሁሉም ትበልጫለሽ። ש [ሺን] 30  ውበት ሐሰት፣ ቁንጅናም አላፊ* ነው፤+ይሖዋን የምትፈራ ሴት ግን ትመሰገናለች።+ ת [ታው] 31  ላከናወነችው ነገር ሽልማት ስጧት፤*+ሥራዎቿም በከተማዋ በሮች ያስመስግኗት።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ ወይም “በነፍሳቸው ለተመረሩትም።”
^ ወይም “ጉዳይ ተሟገት።”
^ ወይም “እጅግ ጥሩ የሆነችን ሚስት።”
^ ወይም “በምታገኘው ገቢ።” ቃል በቃል “ከእጆቿ ፍሬ።”
^ ቃል በቃል “ዳሌዋን በኃይል ትታጠቃለች።”
^ የአመልማሎ ዘንግና እንዝርት፣ ድርና ማግ ለማጠንጠን ወይም ለመሥራት የሚያገለግሉ ቀጫጭን እንጨቶች ናቸው።
^ ቃል በቃል “ድርብ።”
^ ወይም “የውስጥ ልብሶች እየሠራች።”
^ ወይም “በመጪው ጊዜ ላይ ትስቃለች።”
^ ወይም “ፍቅራዊ መመሪያም፤ የታማኝ ፍቅር ሕግም።”
^ ወይም “እጅግ ጥሩ።”
^ ወይም “ከንቱ።”
^ ቃል በቃል “ከእጆቿ ፍሬ ስጧት።”