ምሳሌ 28:1-28

  • ሕግን የማይሰማ ሰው ጸሎት አስጸያፊ ነው (9)

  • ኃጢአቱን የሚናዘዝ ምሕረት ያገኛል (13)

  • ለሀብት የሚጣደፍ ንጽሕናውን ያጎድፋል (20)

  • ወቀሳ ከሽንገላ ይሻላል (23)

  • ለጋስ አይቸገርም (27)

28  ክፉዎች ማንም ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ፤ጻድቃን ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ናቸው።+   በአንድ አገር ውስጥ ሕግ ተላላፊነት* ሲነግሥ ብዙ ገዢዎች ይፈራረቁበታል፤+ይሁንና ጥልቅ ግንዛቤና እውቀት ያለው ሰው በሚያበረክተው እርዳታ ገዢ* ለረጅም ዘመን ይቆያል።+   ችግረኞችን የሚበዘብዝ ድሃ፣+እህሉን ሁሉ ጠራርጎ እንደሚወስድ ዝናብ ነው።   ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ሰዎች ግን በእነሱ ላይ ይቆጣሉ።+   ክፉዎች ፍትሕን መረዳት አይችሉም፤ይሖዋን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር መረዳት ይችላሉ።+   መንገዱ ብልሹ ከሆነ ሀብታም ይልቅንጹሕ አቋም* ይዞ የሚመላለስ ድሃ ይሻላል።+   አስተዋይ ልጅ ሕግን ይጠብቃል፤ከሆዳሞች ጋር የሚወዳጅ ግን አባቱን ያዋርዳል።+   ወለድና+ አራጣ በማስከፈል ሀብት የሚያካብት፣ለድሆች ሞገስ ለሚያሳይ ሰው ያከማችለታል።+   ሕግን ለመስማት አሻፈረኝ የሚል ሰው፣ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።+ 10  ቅኖችን አሳስቶ ወደ መጥፎ መንገድ የሚመራ፣ እሱ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል፤+ነቀፋ የሌለባቸው ሰዎች ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።+ 11  ሀብታም ሰው በገዛ ዓይኖቹ ፊት ጥበበኛ ነው፤+ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ድሃ ግን ማንነቱን ይደርስበታል።+ 12  ጻድቃን ድል ሲያደርጉ ታላቅ ክብር ይሆናል፤ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሰዎች ይሸሸጋሉ።+ 13  የሠራውን በደል የሚሸፋፍን አይሳካለትም፤+የሚናዘዝና የሚተወው ሁሉ ግን ምሕረት ያገኛል።+ 14  ምንጊዜም ተጠንቅቆ የሚኖር* ሰው ደስተኛ ነው፤ልቡን የሚያደነድን ሁሉ ግን ለጥፋት ይዳረጋል።+ 15  ምስኪን በሆነ ሕዝብ ላይ የተሾመ ክፉ ገዢ፣እንደሚያገሳ አንበሳና ተንደርድሮ እንደሚመጣ ድብ ነው።+ 16  ጥልቅ ግንዛቤ የሌለው መሪ ሥልጣኑን አላግባብ ይጠቀማል፤+በማጭበርበር የሚገኝን ትርፍ የሚጠላ ግን ዕድሜውን ያራዝማል።+ 17  የሰው ሕይወት በማጥፋቱ የደም* ባለ ዕዳ የሆነ ሰው መቃብር* እስኪገባ ድረስ ሲሸሽ ይኖራል።+ እንዲህ ያለውን ሰው ማንም አይርዳው። 18  እንከን የለሽ በሆነ መንገድ የሚመላለስ ሰው ይድናል፤+መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ድንገት ይወድቃል።+ 19  መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ የሆኑ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን እጅግ ይደኸያል።+ 20  ታማኝ ሰው ብዙ በረከት ያገኛል፤+ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ንጽሕናውን ማጉደፉ አይቀርም።+ 21  አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤+ሆኖም ሰው ለቁራሽ ዳቦ ብሎ ስህተት ሊፈጽም ይችላል። 22  ቀናተኛ* ሰው ሀብት ለማግኘት ይጓጓል፤ድህነት ላይ እንደሚወድቅ አያውቅም። 23  በምላሱ ከሚሸነግል ይልቅሰውን የሚወቅስ+ የኋላ ኋላ ይበልጥ ሞገስ ያገኛል።+ 24  አባቱንና እናቱን እየዘረፈ “ምንም ጥፋት የለበትም” የሚል ሁሉ+ የአጥፊ ተባባሪ ነው።+ 25  ስግብግብ ሰው* ጠብ ያነሳሳል፤በይሖዋ የሚታመን ግን ይበለጽጋል።*+ 26  በገዛ ልቡ የሚታመን ሁሉ ሞኝ ነው፤+በጥበብ የሚመላለስ ግን ክፉ አያገኘውም።+ 27  ለድሃ የሚሰጥ ሁሉ አይቸገርም፤+እነሱን ላለማየት ዓይኖቹን የሚከድን ግን ብዙ እርግማን ይደርስበታል። 28  ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ሰው ራሱን ይሸሽጋል፤ክፉዎች ሲጠፉ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ዓመፅ።”
ቃል በቃል “እሱ።”
ምሳሌ 2:7 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ፍርሃት ተለይቶት የማያውቅ።”
ወይም “የነፍስ ደም።”
ወይም “ጉድጓድ።”
ወይም “ስግብግብ።”
“እብሪተኛ ነፍስ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ይሰባል።”