ምሳሌ 27:1-27

  • የወዳጅ ወቀሳ ጠቃሚ ነው (5, 6)

  • ልጄ ሆይ፣ ልቤን ደስ አሰኘው (11)

  • ብረት ብረትን ይስላል (17)

  • መንጋህን በሚገባ እወቅ (23)

  • “ሀብት ለዘላለም አይኖርም” (24)

27  ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ፤ቀን የሚያመጣውን* አታውቅምና።+   የገዛ አፍህ ሳይሆን ሌላ ሰው ያመስግንህ፤*የገዛ ከንፈርህ ሳይሆን ሌሎች* ያወድሱህ።+   ድንጋይ ከባድ ነው፤ አሸዋም ሸክም ነው፤የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።+   ንዴት ጨካኝ ነው፤ ቁጣም ጎርፍ ነው፤ይሁንና ቅናትን ማን ሊቋቋም ይችላል?+   ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ወቀሳ ይሻላል።+   የወዳጅ ማቁሰል ከታማኝነት የሚመነጭ ነው፤+የጠላት መሳም ግን የበዛ* ነው።   የጠገበ ሰው* ከማር እንጀራ የሚገኝን ማር አይፈልግም፤*የተራበ* ግን የሚመር ነገር እንኳ ይጣፍጠዋል።   ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን* ሰውከጎጆዋ ወጥታ እንደምትባዝን ወፍ ነው።   ዘይትና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤በቀና ምክር ላይ* የተመሠረተ ጥሩ ወዳጅነትም እንዲሁ ነው።+ 10  መከራ ባጋጠመህ ቀን የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ ትተህወደ ገዛ ወንድምህ ቤት አትግባ፤ሩቅ ቦታ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።+ 11  ልጄ ሆይ፣ ለሚነቅፈኝ መልስ መስጠት እችል ዘንድጥበበኛ ሁን፤+ ልቤንም ደስ አሰኘው።+ 12  ብልህ ሰው አደጋ አይቶ ይሸሸጋል፤+ተሞክሮ የሌለው ሰው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም ይቀበላል።* 13  አንድ ሰው ለማያውቀው ሰው ዋስ ከሆነ ልብሱን ውሰድበት፤ይህን ያደረገው ለባዕድ ሴት* ብሎ ከሆነ መያዣውን ውሰድ።+ 14  ሰው በማለዳ ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን ቢባርክእንደ እርግማን ይቆጠርበታል። 15  ጨቅጫቃ* ሚስት በዝናባማ ቀን ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት።+ 16  እሷን መግታት የሚችል ሁሉ ነፋስን መግታት፣ዘይትንም በቀኝ እጁ መጨበጥ ይችላል። 17  ብረት ብረትን እንደሚስል ሁሉሰውም ጓደኛውን ይስለዋል።*+ 18  የበለስን ዛፍ የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤+ጌታውንም የሚንከባከብ ክብር ይጎናጸፋል።+ 19  ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያንጸባርቅ ሁሉ፣የሰውም ልብ የሌላ ሰው ልብ ነጸብራቅ ነው። 20  መቃብርና የጥፋት ቦታ* አይጠግቡም፤+ልክ እንደዚሁም የሰው ዓይን ፈጽሞ አይጠግብም። 21  ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤+ሰውም በሚቀበለው ውዳሴ ይፈተናል።* 22  ሞኝን ሙቀጫ ውስጥ ከተህ በዘነዘና ብትወቅጠውናእንደ እህል ብታደቀው እንኳሞኝነቱ ከእሱ አይወገድም። 23  የመንጋህን ሁኔታ በሚገባ እወቅ። በጎችህን በደንብ ተንከባከብ፤*+ 24  ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤+አክሊልም* ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም። 25  ሣሩ በቦታው የለም፤ አዲስ ሣርም በቅሏል፤በተራሮች ላይ ያለው ተክልም ተሰብስቧል። 26  የበግ ጠቦቶች ለልብስ፣አውራ ፍየሎችም ለመሬት መግዣ ይሆኑልሃል። 27  ደግሞም አንተንና ቤተሰብህን ለመመገብ፣ልጃገረዶችህንም በሕይወት ለማኖር የሚያስችል በቂ የፍየል ወተት ይኖርሃል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “የሚወልደውን።”
ቃል በቃል “እንግዳ ያመስግንህ።”
ቃል በቃል “የባዕድ አገር ሰዎች።”
“የውሸት፤ የግድ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍስ።”
ቃል በቃል “ይረግጣል።”
ወይም “የተራበች ነፍስ።”
ወይም “የሚሰደድ።”
ወይም “በነፍስ ምክር ላይ።”
ወይም “ይቀጣልም።”
ወይም “ለባዕድ።”
ወይም “ነዝናዛ።”
ቃል በቃል “የጓደኛውን ፊት ይስላል።”
ወይም “ሲኦልና አባዶን።”
ወይም “ሰውም በሚያገኘው ውዳሴ መሠረት ነው።”
ወይም “ልብህን በበጎችህ ላይ አኑር፤ ለበጎችህ ትኩረት ስጥ።”
ወይም “ዘውድም።”