ምሳሌ 5:1-23

  • ሥነ ምግባር ከጎደላት ሴት ራቅ (1-14)

  • ከሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ (15-23)

5  ልጄ ሆይ፣ ጥበቤን ልብ በል። ማስተዋልን በተመለከተ የምሰጠውን ትምህርት በጥሞና አዳምጥ፤*+  2  ይህም የማመዛዘን ችሎታህን እንድትጠብቅ፣በከንፈሮችህም እውቀትን በጥንቃቄ እንድትይዝ ነው።+  3  የጋጠወጥ* ሴት ከንፈር እንደ ማር እንጀራ ያንጠባጥባልና፤+አፏም ከዘይት ይለሰልሳል።+  4  በመጨረሻ ግን እንደ ጭቁኝ ትመርራለች፤+ደግሞም በሁለት በኩል እንደተሳለ ሰይፍ ትሆናለች።+  5  እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ። እርምጃዎቿ በቀጥታ ወደ መቃብር* ይመራሉ።  6  ስለ ሕይወት መንገድ ግድ የላትም። በጎዳናዎቿ ላይ ትባዝናለች፤ ወዴት እንደሚወስዱም አታውቅም።  7  እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤ከምናገረውም ቃል አትራቁ።  8  ከእሷ ራቅ፤ወደ ቤቷም ደጃፍ አትቅረብ፤+  9  ይህም ክብርህን ለሌሎች አሳልፈህ እንዳትሰጥ ነው፤+ቀሪ የሕይወት ዘመንህም በመከራ የተሞላ እንዳይሆን ነው፤+ 10  ደግሞም እንግዳ የሆኑ ሰዎች ጥሪትህን* እንዳያሟጥጡ፣+የለፋህበትንም ነገር የባዕድ አገር ሰው እንዳይወርሰው ነው። 11  አለዚያ በሕይወትህ ማብቂያሥጋህና መላ ሰውነትህ እየመነመነ ሲሄድ ትቃትታለህ፤+ 12  ደግሞም እንዲህ ትላለህ፦ “ምነው ተግሣጽን ጠላሁ! ልቤስ ምነው ወቀሳን ናቀ! 13  የአስተማሪዎቼን ቃል አላዳመጥኩም፤መምህሮቼንም በጥሞና አልሰማሁም። 14  በመላው ጉባኤ መካከል*ሙሉ በሙሉ ልጠፋ ምንም አልቀረኝም ነበር።”+ 15  ከራስህ ጉድጓድ እንዲሁምከገዛ ምንጭህ የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ።*+ 16  ምንጮችህ ወደ ውጭ፣ጅረቶችህም በአደባባይ ሊፈሱ ይገባል?+ 17  ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ።+ 18  ምንጭህ የተባረከ ይሁን፤ከወጣትነት ሚስትህም ጋር ደስ ይበልህ፤+ 19  እሷ እንደምትወደድ ሚዳቋና እንደምታምር የተራራ ፍየል* ናት።+ ጡቶቿ ምንጊዜም ያርኩህ።* ፍቅሯ ምንጊዜም ይማርክህ።+ 20  ልጄ ሆይ፣ ጋጠወጥ* ሴት ለምን ትማርክሃለች?ባለጌ* ሴትንስ ለምን ታቅፋለህ?+ 21  የሰው መንገድ በይሖዋ ዓይኖች ፊት ነውና፤እሱ መንገዱን ሁሉ ይመረምራል።+ 22  ክፉ ሰው የገዛ ጥፋቱ ወጥመድ ይሆንበታል፤ኃጢአቱም እንደ ገመድ ተብትቦ ይይዘዋል።+ 23  ተግሣጽ ከማጣቱ የተነሳ ይሞታል፤በጣም ሞኝ ከመሆኑም የተነሳ መንገድ ይስታል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ ቃል በቃል “ወደ ማስተዋሌ ጆሮህን አዘንብል።”
^ ቃል በቃል “የእንግዳ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
^ ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “ኃይልህን።”
^ ቃል በቃል “በማኅበርና በጉባኤ መካከል።”
^ ወይም “የምንጭህን ንጹሕ ውኃ ጠጣ።”
^ ወይም “ዋልያ።”
^ ወይም “ያስክሩህ።”
^ ቃል በቃል “እንግዳ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።
^ ቃል በቃል “ባዕድ።” ምሳሌ 2:16ን ተመልከት።