በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ድክመትህ ላይ ንገሥ

ድክመትህ ላይ ንገሥ

አውርድ፦

  1. 1. አለ ወይ የሰው ብርቱ፣

    ቢፈለግ ከጥንቱ፤

    ተጉዞ የሚያውቅ፣

    ሳያነክስ ከቶ ሳይወድቅ።

    ሥጋ አሸንፎ፣

    ቢጥልህ አደናቅፎ፤

    ነገን አይቶ ይነሳል፣

    ብልህ ሰው ከስህተቱ ያተርፋል።

    (አዝማች)

    መች ይሠራና ቤት

    ለተሸኘ ክረምት?

    በል አሁን፣ በል ተነስ፤

    ድክመትህ ላይ ንገሥ!

    አምላክህ ነው ዓለት፣

    እስከያዝከው የማይለቅ፤

    እዚያው ቀርተህለት፣

    ለምን ይፈንድቅ ጠላት?

    ድክመትህ ላይ ንገሥ!

  2. 2. ቢመስል የጨለመ፣

    ነገሩ ያከተመ፤

    ይለቃል ሌቱ ቦታ፣

    ለሰማይ ወገግታ።

    ይበራል ቀንዲልህ፤

    ይሖዋ ’ለ ከጎንህ።

    ብቻ በርታ፣ በል ጠንከር፤

    አልፏል ትናንት፣ ነገን ዛሬ ጀምር።

    (አዝማች)

    መች ይሠራና ቤት

    ለተሸኘ ክረምት?

    በል አሁን፣ በል ተነስ፤

    ድክመትህ ላይ ንገሥ!

    አምላክህ ነው ዓለት፣

    እስከያዝከው የማይለቅ፤

    እዚያው ቀርተህለት፣

    ለምን ይፈንድቅ ጠላት?

    (መሸጋገሪያ)

    መርሳት ያለፈውን መተው፣

    ይላል ቃሉ የሚቻል ነው።

    ከልባችን ከሚፈርደው፣

    ይሖዋ ’ይደል

    የሚበልጠው?

    (አዝማች)

    መች ይሠራና ቤት

    ለተሸኘ ክረምት?

    በል አሁን፣ በል ተነስ፤

    ድክመትህ ላይ ንገሥ!

    አምላክህ ነው ዓለት፣

    እስከያዝከው የማይለቅ፤

    እዚያው ቀርተህለት፣

    ለምን ይፈንድቅ ጠላት?

    ድክመትህ ላይ ንገሥ!

    ድክመትህ ላይ ንገሥ!