በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተዋደን እንኑር

ተዋደን እንኑር

አውርድ፦

 1. 1. ስጦታ ነው ያምላክ ስጦታ፣

  የመወደድ፣ የማፍቀር ጸጋ።

  ልብ ለልብ ሲገጥም ምቱ፣

  ደስ ሲል የፍቅር ስሜቱ።

  (አዝማች)

  በሦስት ሲገመድ ነው ትዳር ’ሚዘልቀው፤

  በይሖዋ ነው

  ’ሚሰምረው።

  አስተሳስሮናል እሱ በፍቅር ኪዳን፤

  ተዋደን እንኑር በደስታ፣

  የኔ ስጦታ!

  ስጦታዬ!

 2. 2. ምን ቢከፋ ኑሮ፣

  ፍቅር ይጸናል ሁሉን ችሎ።

  አጠንክሮን ቢያልፍ እንጂ ፈተና፣

  አንለያይም ምንም ቢመጣ፤

  ምንም ቢመጣ!

  (አዝማች)

  በሦስት ሲገመድ ነው ትዳር ’ሚዘልቀው፤

  በይሖዋ ነው

  ’ሚሰምረው።

  አስተሳስሮናል እሱ በፍቅር ኪዳን፤

  ተዋደን እንኑር በደስታ፣

  የኔ ስጦታ!

  ስጦታዬ!

  (መሸጋገሪያ)

  ይሖዋ አጣምሮናል።

  አንድ አድርጎን እሱ፣ ማን ይለየናል?

  እንደ ሞት ብርቱ፣ የጸና ነው ፍቅሬ፤

  የሥጋዬ ሥጋ፣ ሆነሻል አካሌ።

  ሁለመናሽ መልካም ሴት፣ ልዩ ነሽ ለኔ፤

  ሲወድሽ ይኖራል ይህ ልቤ።

 3. 3. ስሚኝ ልግለጽልሽ ፍቅሬን፣

  እንዴት እንደምወድሽ ከልቤ!

  እንኳን ወደድኩሽ! እንኳን ሆንሽ የኔ!

  ደስተኛ ነኝ ስላለሽ ጎኔ፤

  ከጎኔ።

  (አዝማች)

  በሦስት ሲገመድ ነው ትዳር ’ሚዘልቀው፤

  በይሖዋ ነው

  ’ሚሰምረው።

  አስተሳስሮናል እሱ በፍቅር ኪዳን፤

  ተዋደን እንኑር በደስታ፣

  የኔ ስጦታ!

  ስጦታዬ!

  ተዋደን እንኑር በደስታ፣

  የኔ ስጦታ!