በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በነፃ ይቅር እንድል

በነፃ ይቅር እንድል

አውርድ፦

 1. 1. ሰነበተ ቂም ይዞ ሆዴ፤

  አልወጣ አለኝ ከሐሳቤ፤

  በቃ፣ አቃተኝ ታግዬ።

  አልጠፋኝም ይቅር ማለቴ፣

  እንደሚበጀኝ ሁሉን መርሳቴ፤

  ሰበብ ያቀርባል እንጂ ውስጤ።

  (ቅድመ አዝማች)

  እምቢ ካለማ ካቃተው ልቤ፣

  ልለምነው አምላኬን ተንበርክኬ፤

  ይገባዋል ይህ ስሜቴ።

  (አዝማች)

  ልለምነው፤

  አሁንስ ካቅሜ በላይ ነው።

  ባክህ፣ አበርታኝ አምላኬ

  ይቅር እንድል ዛሬ፤

  ትዝ እንዲለኝ እርዳኝ

  መሐሪነትህ፣ ሰፊው ይቅርታህ።

  ባክህ፣ ኃይል ስጠኝ አምላኬ

  ይቅር እንዲል ልቤ፤

  በነፃ ’ንዲል።

 2. 2. ረሳሁት ስል ብዙ ሞክሬ፤

  ደግሞ ድቅን ይላል ፊቴ፤

  ትቶ ቢተው ምናለ ውስጤ።

  ቂም ያልያዘ፣ ይቅር ያለ ሰው

  አያስብም በደሉን መልሶ፤

  እንዲህ ነው መርሳት ጨርሶ።

  (ቅድመ አዝማች)

  እምቢ ካለማ ካቃተው ልቤ፣

  ልለምነው አምላኬን ተንበርክኬ፤

  ይገባዋል ይህ ስሜቴ።

  (አዝማች)

  ልለምነው፤

  አሁንስ ካቅሜ በላይ ነው።

  ባክህ፣ አበርታኝ አምላኬ

  ይቅር እንድል ዛሬ፤

  ትዝ እንዲለኝ እርዳኝ

  መሐሪነትህ፣ ሰፊው ይቅርታህ።

  ባክህ፣ ኃይል ስጠኝ አምላኬ

  ይቅር እንዲል ልቤ፤

  ይቅር እንድል፣

  በነፃ ’ንድል፤

  ይቅር እንድል፣

  በነፃ ’ንድል።