በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጉልበትህን ስጠው ላምላክህ

ጉልበትህን ስጠው ላምላክህ

አውርድ፦

 1. 1. ያኔ ልጅ ሳለን በቅን ልቦና፣

  ቀላል ነበር ማድረግ ቀና።

  ያ ደስታችን ለስብከት ስንወጣ፤

  ሳንጸልይ አንተኛም ማታ።

  (ቅድመ አዝማች)

  ግን ሁሌ ልጅ ሆኖ አይኖር፣ አድገህ ስታየው፤

  ያ ደስታህ፣ ያገልግሎት ፍቅርህ አለ ወይ እንደ ቀድሞው?

  ወጣት ሳለህ አሁን ዛሬ፣ ከፍ ሲልም ዕድሜህ፣

  መቼም ይሖዋን አትተው፤

  ሕይወትህን ስጠው።

  (አዝማች)

  ላንተ ’ሚሆን ቦታ አለ በቤቱ፤

  ውድ ነህ በፊቱ።

  መስጠት ትችላለህ ብዙ፣ ገና ብዙ፤

  ይሖዋ ያውቅሃል፤

  ውድ ነህ ለሱ።

 2. 2. ይህ ወጣትነት ስሜቱ እንግዳ፣

  በፈተና የተሞላ።

  ግራ ገብቶህ መላው ሲጠፋህ፤

  ንገረው፣ ይደርስልሃል።

  (ቅድመ አዝማች)

  ለውሳኔ ደርሰህ አድገህ፣ ጥበብ ሲያስፈልግህ፤

  ቃሉን ስማ፣ ላንተው ነው የሚመክርህ።

  ወጣት ሳለህ አሁን ዛሬ፣ ከፍ ሲልም ዕድሜህ፣

  መቼም ይሖዋን አትተው፤

  ሕይወትህን ስጠው።

  (አዝማች)

  ላንተ ’ሚሆን ቦታ አለ በቤቱ፤

  ውድ ነህ በፊቱ።

  መስጠት ትችላለህ ብዙ፣ ገና ብዙ፤

  ይሖዋ ያውቅሃል፤

  ውድ ነህ ለሱ።

  (መሸጋገሪያ)

  ጉልበትህን ስጠው ላምላክህ።

  አትጠራጠር፤ አይቆጭህም ታያለህ።

  (አዝማች)

  ላንተ ’ሚሆን ቦታ አለ በቤቱ፤

  ውድ ነህ በፊቱ።

  መስጠት ትችላለህ ብዙ፣ ገና ብዙ፤

  ይሖዋ ያውቅሃል፤

  ውድ ነህ ለሱ።

  (መሸጋገሪያ)

  ጉልበትህን ስጠው ላምላክህ።

  አትጠራጠር፤ አይቆጭህም ታያለህ።

  ጉልበትህን ስጠው ላምላክህ።

  አትጠራጠር፤ አይቆጭህም ታያለህ።