በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደፋር እና ብርቱ

ደፋር እና ብርቱ

አውርድ፦

  1. 1. ጎህ ባይቀድም

    ጀምበር ወጥታ፣

    ከ’ንቅልፏ ተነስታ፣

    ልታቀርብ ምልጃ

    ስለ ልጆቿ፣

    እሱን ልትል አደራ።

    አልገፋ ሲል ኑሮ፣

    ተስፋ አትቆርጥም ቶሎ።

    አይጠፋም ከልቧ

    ያ መዝሙር፣ መቼም ከሐሳቧ።

    (አዝማች)

    ‘እረዳሻለሁ፤

    አይዞሽ፣ አትፍሪ።

    አለሁ ከጎንሽ፤

    በርቺ፣ ጠንክሪ።’

    ስትዘምር በልቧ

    ትላለች ለራሷ፦

    “አዎ፣ ያጸናኛል፤

    ያጠነክረኛል።”

    (መሸጋገሪያ)

    ትወጣለች ማልዳ፣

    ታጥቃ ለሥራ፣

    ቀንቶኝ ብመለስ ብላ።

    አነሰም በዛ፣

    አትሰጋም እሷ፤

    አሉላት ወዳጆቿ።

  2. 2. የንስርን

    ብርታት ሰጥቷት፣

    አትታክት በራ፤

    ያ ሁሉ ሥራ፣

    እረፍት የላት ላፍታ።

    ደፋ ቀና ነው ውሎዋ፤

    ብታዝንም፣ ብትከፋ

    እጅ አትሰጥም በቃኝ ብላ።

    ብርታት ይሆናታል

    ያ መዝሙር፣ ያጠነክራታል።

    (አዝማች)

    ‘እረዳሻለሁ፤

    አይዞሽ፣ አትፍሪ።

    አለሁ ከጎንሽ፤

    በርቺ፣ ጠንክሪ።’

    ስትዘምር በልቧ

    ትላለች ለራሷ፦

    “አዎ፣ ያጸናኛል፤

    ያጠነክረኛል።”

    “አዎ፣ ያጸናኛል፤

    ያጠነክረኛል።”