በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እይማ

እይማ

አውርድ፦

 1. 1. ይታየኛል አዲስ ዓለም፣

  በደስታ ስንኖር ዘላለም።

  እይማ፣

  ደስ ሲል

  ያ ዓለም!

 2. 2. ሕልም አይደለም አትጠራጠር፤

  ይሖዋ ያለው ሁሉ አይቀር።

  ይፈጸማል፤

  ይህ ሁሉ

  ይሆናል።

  (አዝማች)

  እይማ፣

  ሁሉም ቤት ሳቅ ብቻ ሲሰማ!

  እይማ፣

  አምላክ ያሰበልን ይህ ነው ለካ!

 3. 3. ሞት ነጥቆን አብረውን የሌሉ፣

  ይነሳሉ፤ ያኔ ይነቃሉ።

  ይታይህ፣

  የሞቱት

  ሲነሱ።

 4. 4. ያ ሁሉ ችግር፣ ያ አበሳ፣

  ያም ዘመን አልፎ እንዲህ ተረሳ!

  ይታይህ፣

  ያ ሁሉ

  ሲረሳ!

  (አዝማች)

  እይማ፣

  ሁሉም ቤት ሳቅ ብቻ ሲሰማ!

  እይማ፣

  አምላክ ያሰበልን ይህ ነው ለካ!

 5. 5. እርግጠኛ ነኝ በበኩሌ፣

  እውን ሆኖ ’ንደማየው ባይኔ።

  (መሸጋገሪያ)

  ጠብ አይል

  የሱ ቃል፤

  ይፈጸማል።

  ብቻ ለማየት ያብቃን

  ያኔ!

 6. 6. ይታይህ አዲስ ዓለም፣

  በደስታ ስንኖር ዘላለም።

  እይማ፣

  ደስ ሲል

  ያ ዓለም!