በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ድፍረት ስጠኝ

ድፍረት ስጠኝ

(2 ነገሥት 6:16)

አውርድ፦

 1. 1. ፍርሃት፣ ስጋት አለኝ፤

  የነገን አላውቅም።

  ግን አንተ ትመራኛለህ፤

  ከ’ኔ ጋር ነህ ሁሌም።

  ሕይወት ፈተና ነው።

  ግን ይህን አውቃለሁ፦

  አንተ ምንጊዜም ታማኝ ነህ፤

  ሕይወቴ በ’ጅህ ነው።

  (አዝማች)

  ይሖዋ የ’ምነት ዓይን ስጠኝ፤

  ደፋር ልሁን እርዳኝ።

  ከሚቃወሙን ይበልጣሉ፤

  ከጎናችን ያሉ።

  ደፋር ልሁን እርዳኝ፤

  ድፍረት ያጸናኛል።

  ይሖዋ ድፍረት ስጠኝ፤

  ባንተ ድል ይገኛል።

 2. 2. ማንም ሰው ይፈራል፤

  እኔም ደካማ ነኝ።

  አንተ ግን ሁሌም ኃያል ነህ፤

  ዓለት፣ ምሽግ ሆንከኝ።

  ደፋር ልሁን እርዳኝ፤

  ልቤ ጽኑ ይሁን።

  አይደለም ዘላቂ ጉዳት

  እስርም ሆነ ሞት።

  (አዝማች)

  ይሖዋ የ’ምነት ዓይን ስጠኝ፤

  ደፋር ልሁን እርዳኝ።

  ከሚቃወሙን ይበልጣሉ፤

  ከጎናችን ያሉ።

  ደፋር ልሁን እርዳኝ፤

  ድፍረት ያጸናኛል።

  ይሖዋ ድፍረት ስጠኝ፤

  ባንተ ድል ይገኛል።

  (አዝማች)

  ይሖዋ የ’ምነት ዓይን ስጠኝ፤

  ደፋር ልሁን እርዳኝ።

  ከሚቃወሙን ይበልጣሉ፤

  ከጎናችን ያሉ።

  ደፋር ልሁን እርዳኝ፤

  ድፍረት ያጸናኛል።

  ይሖዋ ድፍረት ስጠኝ፤

  ባንተ ድል ይገኛል።

  ይሖዋ ድፍረት ስጠኝ፤

  ባንተ ድል ይገኛል።