በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በእምነት ይሳካል

በእምነት ይሳካል

አውርድ፦

 1. 1. አርፎ አያውቅ ልቤ እንደጠየቀ፣

  እውነትን ሰማና ተማረከ።

  እንደሰማ ተማረከ።

  መልሱን አገኘሁ፣ አረፈ ልቤ።

  እፎይ አልኩ ተገላገልኩ ከሐሳቤ።

  ተገላገልኩ ከጭንቀቴ።

  (አዝማች)

  ጉዞው አይሆን አልጋ ባልጋ፣

  በ’ምነት ግን ይሳካል።

  ግራ ሲገባኝ፣ መውጫ ሳጣ

  በእምነት ይሳካል።

  በእምነት ኃይል።

 2. 2. ተነሳሳ ልቤ ለመንገር ቃሉን፣

  የተረዳሁትን፣ ያወቅኩትን።

  ለመናገር

  የተማርኩትን።

  በልቤ አምቄ ልይዘው አልችልም።

  እምነቴ ግድ ይለኛል፤ ዝም አልልም።

  አውጃለሁ፤ ዝም አልልም።

  (አዝማች)

  ጉዞው አይሆን አልጋ ባልጋ፣

  ይ’ን ግን አልዘነጋም።

  ግራ ሲገባኝ፣ መውጫ ሳጣ

  በእምነት ይሳካል።

  በእምነት ኃይል።

  (መሸጋገሪያ)

  ከባድ ችግር ገጥሞኝ የተከፋሁ ’ለት

  መጸለይ ነው ’ሚረዳኝ፣ ይሖዋን ሙጥኝ ማለት።

  አውቃለሁ እንደሚያበረታኝ፣

  ከቆምኩ ባምላክ ታምኜ፤

  ምንም ነገር ቢመጣ

  እንደሚሆን ጎኔ።

  (አዝማች)

  ጉዞው አይሆን አልጋ ባልጋ፣

  ይ’ን ግን አልዘነጋም።

  ግራ ሲገባኝ፣ መውጫ ሳጣ

  በእምነት ይሳካል።

  (አዝማች)

  ጥርጣሬ የለ ልቤ፣

  በእምነት ይሳካል።

  ግራ ሲገባኝ፣ መውጫ ሳጣ

  በእምነት ይሳካል።

  በእምነት ኃይል።