በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አሁኑኑ

አሁኑኑ

አውርድ፦

 1. 1. ያለም ፍጻሜ ምልክቱ

  ተፈጽሟል ትንቢቱ።

  የእረፍት አይደለም ሰዓቱ፤

  አልቆለታል ሥርዓቱ።

  የሚባክን ጊዜ የለንም፤

  እናውጅ ያምላክን ስም፤

  እንደሚመጣ መንግሥቱ

  እንናገር መል’ክቱን።

  (አዝማች)

  አሁኑኑ

  እንስበክ ቃሉን፤

  ያላንዳች ፍርሃት እናውጅ ስሙን።

  ፍጻሜው ደርሷል፤

  እንስበክ ቃሉን፤

  ጊዜው ሳያልቅብን፣ አሁን።

 2. 2. ጊዜው ፈጥኖ ያልፋል፤ ይነጉዳል።

  ሥራው በቃ ይባላል።

  ካሁኑ በትጋት እንሥራ

  እንዳይቆጨን በኋላ።

  ያኔ ተሻግረን ይህን ዘመን

  ስናስብ መለስ ብለን

  ‘ለይሖዋ ምርጣችንን፣

  ሁሉን ሰጠን’ ’ንላለን።

  (አዝማች)

  አሁኑኑ

  እንስበክ ቃሉን፤

  ያላንዳች ፍርሃት እናውጅ ስሙን።

  ፍጻሜው ደርሷል፤

  እንስበክ ቃሉን፤

  ጊዜው ሳያልቅብን፣ አሁን።

  (መሸጋገሪያ)

  በብዙ ደጋፊ ታጅበን

  በጽናት እንሮጣለን።

  ዙሩን ስንጨርስ በርትተን

  ድል እንቀዳጃለን።

  (አዝማች)

  አሁኑኑ

  እንስበክ ቃሉን፤

  ያላንዳች ፍርሃት እናውጅ ስሙን።

  ፍጻሜው ደርሷል፤

  እንስበክ ቃሉን፤

  ጊዜው ሳያልቅብን፣ አሁን።