በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በእምነት ዓይኔ

በእምነት ዓይኔ

(መዝሙር 27:13)

አውርድ፦

 1. 1. አንበሳውን አልፈራም፣

  የጠላትን ድንፋታ።

  የይሖዋን እጅ ይዤ፣

  አይሸበርም ልቤ።

  ከጎኔ ነው እሱ፣ ሁሌም።

  (አዝማች)

  በ’ምነት ዓይኔ፣ ጨለማውን ገፍፌ

  በ’ምነት ዓይኔ፣ አየሁ አሻግሬ።

  በይሖዋ በረታሁ፤

  ከሰመ ፍርሃቴ።

  አምላኬን አየሁት ከጎኔ፣

  በ’ምነት ዓይኔ።

 2. 2. ያምላካችን ወዳጆች፣

  የጥንቶቹ ታማኞች፣

  በተስፋው ቃል አምነው

  በፈተና ጸኑ።

  ዳግም ሕያው ይሆናሉ።

  (አዝማች)

  በ’ምነት ዓይኔ፣ ጨለማውን ገፍፌ

  በ’ምነት ዓይኔ፣ አየሁ አሻግሬ።

  በይሖዋ በረታሁ፤

  ከሰመ ፍርሃቴ።

  አምላኬን አየሁት ከጎኔ፣

  በ’ምነት ዓይኔ።

  (መሸጋገሪያ)

  በእምነት ኃይል ተራራው ተገፋ፤

  በእምነት ዓይን ታየኝ ተስፋው።

  አምላኬ ሆይ፣

  ባልኖር ፍቅርህን አምኜ፤

  ምን ይውጠኝ ነበር ዛሬ!

 3. 3. ተስፋው እውን ነው ለኔ፤

  አይጠፋም ካሳቤ።

  ቅርብ ነው ቀኑ፤

  አይዘገይም እሱ።

  እጸናለሁ ’ስኪፈጸም ቃሉ።

  (አዝማች)

  በ’ምነት ዓይኔ፣ ጨለማውን ገፍፌ

  በ’ምነት ዓይኔ፣ አየሁ አሻግሬ።

  በይሖዋ በረታሁ፤

  ከሰመ ፍርሃቴ።

  አምላኬን አየሁት ከጎኔ፣

  በ’ምነት ዓይኔ።

  በ’ምነት ዓይኔ!

(በተጨማሪም ዕብ. 11:1-40⁠ን ተመልከት።)