በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አንድ ቤተሰብ

አንድ ቤተሰብ

አውርድ፦

 1. 1. ተሳፍረን በላይ በሰማይ፣

  አድማስ ተሻግረን መጥተናል፤

  ሐሳባችንን

  ባምላክ ላይ ጥለን፣

  እንደሚረዳን ታምነን።

  አይተናል የሱን እጅ ሲባርከን፤

  ሥራችን ሲቃናልን።

  እናንተን ብለን ነው እዚህ የመጣነው፤

  የጠራን ፍቅር ነው።

  (አዝማች)

  እኛ የይሖዋ ሕዝብ፣

  አንድ ነን፤ አንድ ቤተሰብ።

  ድንበር አራርቆን እንጂ

  አንድ ነን፤

  አንድ ቤተሰብ።

 2. 2. መጥታችሁ ስትቀበሉን፣

  ደስ አለን ስናይ ፊታችሁን፤

  ሰዓቱ ደርሶ፣ አብረን ዘምረን

  ስንማር ውለን ቀኑን፣

  ደስ ብሎን መጣን ሁሉ ሰምሮልን።

  ይመስገን አምላካችን።

  በሱ ተአምር ነው እንዲህ የተዋደድነው፤

  ውዳሴ ሲያንሰው ነው።

  (አዝማች)

  እኛ የይሖዋ ሕዝብ፣

  አንድ ነን፤ አንድ ቤተሰብ።

  ድንበር አራርቆን እንጂ

  አንድ ነን፤

  አንድ ቤተሰብ።

 3. 3. ብንርቅም ከወዳጅ ዘመድ፣

  ብንሆንም ላገሩ አዲስ

  ሕዝቡ ግን ገር ነው፤ የዋህ፣ ልበ ቅን፣

  የተጠማ እውነትን።

  ቤተሰብ አገኘን የሚወዱን፤

  ፍቅር አስረሳን ሁሉን።

  ምን ቢርቅ አገሩ፣ ምን ቢለይ ባሕሉ

  ወንድሞች አሉልን።

  (መሸጋገሪያ)

  የትም ብንሄድ፣

  ወዳጅ፣ ቤተሰብ አለን ባለም ዙሪያ፤

  ከማሊ ’ስከ ሜክሲኮ፣

  ከጃፓን ’ስከ ጃማይካ!

  (አዝማች)

  እኛ የይሖዋ ሕዝብ፣

  አንድ ነን፤ አንድ ቤተሰብ።

  ድንበር አራርቆን እንጂ

  አንድ ነን፤

  አንድ ቤተሰብ።

  ቋንቋ፣ ብሔር ሳይለየን

  አንድ ነን፤ አንድ ቤተሰብ።

  ግልጽ አይደለም ወይ ላየን ሰው

  ፍቅራችን፣ አንድ መሆናችን።

  ፊጂ፣ ታሂቲና ደቡብ አፍሪካ

  ኮንጎ፣ ብሪታንያና ካናዳ

  አዘርባጃን፣ አንጎላና ኢስቶኒያ

  አንድ ነን፤ አንድ ቤተሰብ።