በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ

ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ

አውርድ

 1. 1. ምን ይሻላል? ማን ይረዳኛል?

  አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ምን ጉዳት አለው?

  መቃወም የለብኝም ሁሉንም ነገር።

  ግን ልክ የሆነው የቱ ነው? የቱን ልከተል?

  እንዴት ላድርግ? ምን ይሻለኛል?

  ጎጂ ሊሆን ይችላል፣ አደጋው ብዙ፤

  ይህ ሁሉ ነገር አስፈሪ ነው መዘዙ።

  ታዲያ የቱ ነው ’ሚበጀኝ? ይሖዋ ’ባክህ አንተ ምራኝ።

  (አዝማች)

  ማሳሰቢያዎችህ ለኔ ውድ ናቸው።

  አይሰለቸኝ፣ ሁሌም እታዘዘዋለሁ።

  ቃልህ ያስተማረኝ ነገር እንዲገባኝ እርዳኝ እባክህ።

 2. 2. ገብቶኛል ’ምትሻው። እጠነቀቃለሁ።

  የሌሎች ስሜት እንዲጎዳ ’ልፈልግም።

  ሆኖም በዚህ ሰበብ ችግር ውስጥ አልገባም።

  መምረጥ ያለብኝ ገብቶኛል፤ ጥሩው፣ የሚያዋጣኝ።

  (አዝማች)

  ማሳሰቢያዎችህ ለኔ ውድ ናቸው።

  ያጸኑኛል፤ ዓይኔንም ይገልጡልኛል።

  ቃልህ ያስተማረኝ ነገር እንዲገባኝ እርዳኝ እባክህ።

  (አዝማች)

  ማሳሰቢያዎችህ ለኔ ውድ ናቸው።

  ያጸኑኛል፤ ዓይኔንም ይገልጡልኛል።

  ሌት ተቀን ሳነበው ብርሃን ይታየኛል።

  ኃያልነትህን ሳስብ ’በረታለሁ።

  ቃልህ ያስተማረኝ ነገር እንዲገባኝ እርዳኝ እባክህ።