በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ያ አዲስ ዘመን

ያ አዲስ ዘመን

አውርድ፦

 1. 1. ያን ጊዜ ሳስብ ይህ ነው ምኞቴ፣

  ሁሉ አዲስ ሆኖ ሲፈጸም ሕልሜ፤

  በለምለም ሜዳ ላይ

  ልጆች ቦርቀው ’ሚያድጉበት ጊዜ።

  ከስፍራው ጠፍቶ ክፋት ሁሉ፣

  ቅኖች ብቻ ምድርን ወርሰው ሲኖሩ፤

  ሰላም፣ ፀጥታ ሰፍኖ፣

  ይታየኛል ሕይወት እንዲህ ሆኖ።

  መች ይሄን ብቻ፣

  ብዙ እናያለን ገና፤

  ያ ዘመን ሲመጣ።

  (አዝማች)

  መልሕቅ ሆነን ይህ ተስፋ፣

  እምነት ሲያንሰን የሚያበረታ።

  ናፈቅን ብሩህ ቀን በተስፋ።

  ማየት እንጓጓለን

  ያንን አዲስ ዘመን።

 2. 2. ያን ጊዜ ሳስብ ይህ ነው ምኞቴ፣

  በለምለሙ አምባ ላይ ባበቦች መሃል

  መኖር ቤት ሠርቼ።

  አንድ ቀን ማዶ ሳይ ከደጄ፣

  ቆሜ ቀረሁ ፈዝዤ፤

  ሞት የነጠቀኝ ያ ወዳጄ

  ሲመጣ አይቼ፤

  ተቃቅፈን ስንላቀስ ታየኝ ያኔ።

  ጠላት ሞት እንኳ

  ድል ይደረጋል፤

  ያ ዘመን ሲመጣ።

  (አዝማች)

  መልሕቅ ሆነን ይህ ተስፋ፣

  እምነት ሲያንሰን የሚያበረታ።

  ናፈቅን ብሩህ ቀን በተስፋ።

  ማየት እንጓጓለን

  ያንን አዲስ ዘመን።

  (መሸጋገሪያ)

  ካፉ የሚወጣው ቃል

  ከንቱ አይቀርም፤ ይፈጸማል።

  እንደ ፈቃዱ ይሆናል፤

  ፍጥረት ሁሉ ምኞቱ ይረካል።

  (አዝማች)

  መልሕቅ ሆነን ይህ ተስፋ፣

  እምነት ሲያንሰን የሚያበረታ።

  ናፈቅን ብሩህ ቀን በተስፋ።

  ማየት እንጓጓለን

  ያንን አዲስ ዘመን።

  ያንን አዲስ ዘመን።

  ያንን አዲስ ዘመን።

  ያንን አዲስ ዘመን።