በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ያንተው ትሁን ነፍሴ

ያንተው ትሁን ነፍሴ

አውርድ፦

 1. 1. በተንጣለለው ሰማይ፣

  ማታ ከዋክብቱን ሳይ፣

  ባሰብኩህ ቁጥር ይነካል ልቤ፤

  በሥራህ ተደምሜ።

 2. 2. ላመልክህ በፈቃዴ

  ሰጥቻለሁ ሕይወቴን፤

  ቃል እገባለሁ ልቆም ከጎንህ፣

  ዘላለም ልኖር ቤትህ።

  (አዝማች)

  በተስፋ ፈውሰህ

  አጽናናኸኝ፤

  ካፈር አነሳኸኝ።

  ልጅህን ሰጥተኸኝ፣

  ሞቶ ለኔ፣

  አልኖርም ለራሴ፤

  ያንተው ትሁን ነፍሴ።

 3. 3. ጎህ ሲቀድ በማለዳ፣

  ሞቅ ሲል ፀሐይ ወጥታ፣

  ፍቅርህን ሳስብ ይነካል ልቤ፤

  ውለታህን አስቤ።

  (አዝማች)

  በተስፋ ፈውሰህ

  አጽናናኸኝ፤

  ካፈር አነሳኸኝ።

  ልጅህን ሰጥተኸኝ፣

  ሞቶ ለኔ፣

  አልኖርም ለራሴ፤

  ያንተው ትሁን ነፍሴ።

  (አዝማች)

  በተስፋ ፈውሰህ

  አጽናናኸኝ፤

  ካፈር አነሳኸኝ።

  ልጅህን ሰጥተኸኝ፣

  ሞቶ ለኔ፣

  ያንተው ትሁን ነፍሴ፤

  ያንተው ትሁን ነፍሴ።