በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ስብሰባ የሚያስገኘው ደስታ

ስብሰባ የሚያስገኘው ደስታ

አውርድ፦

 1. 1. ሙዚቃው ሳይጀምር፣ ሳይደርስ ሰዓቱ

  ገና ካሁኑ፣ ደምቋል ዕለቱ።

  ዓለም ሲታመስ እኛ ሰላም ነን።

  አሁን ጀመርን ስብሰባችንን።

  (አዝማች)

  ወንድሞቼ፣ እህቶቼ፣ ቤተሰቤ ናችሁ።

  ገና ሳላውቃችሁ ነው ልቤ የወደዳችሁ።

  ወንድሞቼ፣ እህቶቼ፣ ቤተሰቤ ናችሁ።

  ገና ሳላውቃችሁ ነው ልቤ የወደዳችሁ።

 2. 2. በአምላክ ሕዝቦች ተከብቤ፣ ዙሪያዬ ሆነው

  ባንተዋወቅም ገረመኝ ፍቅራቸው፤

  ባላውቃቸውም ወደድኳቸው።

  ከርቀት ሲውለበለብ እጃቸው

  አቤት ማማራቸው!

  የደስታ ስሜት ውስጤን ወረረው፤

  እንባዬ መጣ ሳላስበው።

  (አዝማች)

  ወንድሞቼ፣ እህቶቼ፣ ቤተሰቤ ናችሁ።

  ገና ሳላውቃችሁ ነው ልቤ የወደዳችሁ።

  ወንድሞቼ፣ እህቶቼ፣ ቤተሰቤ ናችሁ።

  ገና ሳላውቃችሁ ነው ልቤ የወደዳችሁ።

  (መሸጋገሪያ)

  ሳንለያይ፣

  ተባብረን ባንድ ላይ።

  ተደጋግፈን

  እንጸናለን፤ ድል እናደርጋለን።

  (አዝማች)

  ወንድሞቼ፣ እህቶቼ፣ ቤተሰቤ ናችሁ።

  ገና ሳላውቃችሁ ነው ልቤ የወደዳችሁ።

  ወንድሞቼ፣ እህቶቼ፣ ቤተሰቤ ናችሁ።

  ገና ሳላውቃችሁ ነው ልቤ የወደዳችሁ።

  ገና ሳላውቃችሁ ነው ልቤ የወደዳችሁ።