በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ቤተሰብ

የይሖዋ ቤተሰብ

አውርድ፦

 • ባለኖታ

 1. 1. ቀና ሰው፣ መቼም የማይከዳ፣

  የት አለ ባለም ላይ እውነተኛ ወዳጅ!

  ያልሄድኩበት የለም ቅኖችን ፍለጋ፣

  ባገኘው ብዬ ፍቅር ካለማ።

 2. 2. ሕልሜ ተሳካ የትናንቱ፤

  አምላክ አይቶ መሻቴን አስጠጋኝ ከቤቱ።

  ተካሰ ልቤ ፍቅር የተራበው፣

  ምን ወዳጅ ብቻ፣ ይኸው ቤተሰብ አገኘሁ!

  (መሸጋገሪያ)

  ወንድም፣ እህት አለኝ ዛሬማ፣ ተካስኩ በነሱ፤

  እናትና አባትም አገኘሁ ብዙ።

  ከዘር ከብሔር ሁሉ ቤቱ ሰበሰበን፤

  እንዴት ደስ ይላል የይሖዋ ቤተሰብ!

 3. 3. አቤት ፍቅራችን እውነተኛ፣

  ይህን ፍቅር ቀምሰናል፣ ታድለናል እኛ።

  ባለም ላይ እንዲህ ዓይነት ሕዝብ የት አለ?

  እንዴት ደስ ይላል የይሖዋ ቤተሰብ!

  (መሸጋገሪያ)

  ከዘር ከብሔር ሁሉ ቤቱ ሰበሰበን፤

  እንዴት ደስ ይላል የይሖዋ ቤተሰብ!

 4. 4. ደጉ ይሖዋ ዘርግቶ እጆቹን፣

  ተቀብሎናል ቤቱ ክፍት አድርጎ ደጁን።

  አቤት ያኔማ ስንኖር ዘላለም፣

  ገና ይደምቃል የይሖዋ ቤተሰብ!

  አዎ፣ የይሖዋ ቤተሰብ።

  ቤተሰብ።

  ቤተሰብ።