በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም

ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም

አውርድ፦

 1. 1. ፍርሃት ነግሦ በልቤ፣

  የስጋት ነበረ ሕይወቴ።

  አሁን አለፈ ያ ጊዜ፤

  ታሪክ ሆኗል ጭንቀቴ።

  ኃያሉን አምላክ አውቄ፣

  በክንፎቹ ሥር ሆኜ፣

  ፍቅሩን ተማምኜ።

  (አዝማች)

  እሱ’ኮ ነው

  ደክሞኝ ያበረታው ክንዴን፤

  ጨንቆኝ ያጽናናው ልቤን፣

  ከማጥ ያወጣት ነፍሴን።

  በሱ ሁሉን አለፍኩ፤

  ፍርሃቴን አሸነፍኩ፤

  በሱ ታምኜ እፎይ አልኩ።

  ይሖዋ አብሮኝ ነው ሁሌም።

  እጄን ይዞ

  መንገድ መራኝ።

  ብርሃን አየ ዓይኔ።

  አይተወኝም፤

  ይህን አምናለሁ፤

  አይለይም ከኔ።

 2. 2. “ማንም የለኝም”

  ብለህ አታስብ ከቶ፤

  አለ አብሮህ።

  ካጠገብህ ነው፤

  ብትወድቅ እንኳ ያነሳሃል።

  አዎ፣ ይረዳሃል።

  (አዝማች)

  እሱ’ኮ ነው

  ደክሞህ ብርታት የሚሰጥህ፤

  ጨንቆህ የሚያረጋጋህ፣

  ከማጥ ውስጥ የሚያወጣህ።

  በሱ ሁሉ ያልፋል፤

  ፍርሃትህ ይጠፋል፤

  እሱን አምነህ ልብህ ያርፋል።

  ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም።

  ሁሌም፣ ሁሌም።

  ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም።

  አንተንም እንደኔ

  ይመራሃል፤

  መንገድ ያሳይሃል።

  ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም።

  አይተወንም፤

  ሕዝቡን አይጥልም፤

  ፊቱን አይሰውርም።

  (አዝማች)

  እሱ ነው

  ደክሞኝ ያበረታው ክንዴን፤

  ጨንቆኝ ያጽናናው ልቤን፣

  ከማጥ ያወጣት ነፍሴን።

  በሱ ሁሉን አለፍኩ፤

  ፍርሃቴን አሸነፍኩ፤

  በሱ ታምኜ እፎይ አልኩ።

  ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም።

  ሁሌም፣ ሁሌም።

  ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም።

  ሁሌም፣ ሁሌም።

  ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም።