በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እዚያው አልቀርም

እዚያው አልቀርም

አውርድ፦

 1. 1. ብቸኝነት ልቤን ጎዳው፣ አምላኬ ሆይ።

  ጥፋቴ ገብቶኛል፤ በድያለሁ።

  ተስፋ ቆርጫለሁ፣ ከፍቶኛል፣ ደክሜያለሁ።

  ወዳንተ መመለስ ’ፈልጋለሁ።

  (አዝማች)

  ትዝ ይለኛል ያስተማርከኝ፣ አልዘነጋሁም።

  ቃልህ በልቤ ነው፣ አልረሳሁም።

  እነሳለሁ ብወድቅም፣ ብደናቀፍም፣

  እዚያው አልቀርም።

 2. 2. የሚወዱኝ፣ ’ሚያስቡልኝ

  ሰዎች የማገኘው

  ካንተ ታማኝ ሕዝቦች መሐል ነው።

  መንገዱን ያሳየኝ፣ ያንተ ቃል ይሁን መብራቴ።

  ከሕዝብህ ጋር መሆን ነው ምኞቴ።

  (መሸጋገሪያ)

  ’ሚታየው ሁሉ፣ ’ሚሰማው ሁሉ አስጨናቂ ሆኗል።

  መጨረሻው ቀርቧል።

  (አዝማች)

  ይሖዋ ልመናዬን፣ ስማ ጸሎቴን።

  ’ባክህ እርዳኝ፣ ታውቃለህ ችግሬን።

  ነግረኸኛል ብወድቅም ብዙ ጊዜ፣

  እዚያው አልቀርም።

  (መሸጋገሪያ)

  አምላክ የሚያስፈልገኝን፣ ያውቃል የሚያበረታኝን።

  እሱ ነው ውስጤን የሚያውቀው፣ ደካማ መሆኔን።

  ልቤን ያያል፣ መልካም ጎኔን።

  (አዝማች)

  ያጣሁትን ፍቅር ለማግኘት ስብሰባ ’ሄዳለሁ።

  ወዳምላኬ ቤት ’መጣለሁ።

  እነሳለሁ ብወድቅም፣ ብደናቀፍም፣ እዚያው አልቀርም።

  እዚያው አልቀርም።