በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ውዴ፣ የኔ

ውዴ፣ የኔ

አውርድ፦

 1. 1. ፍቅሬ ሆይ፣

  የኔ፣ የብቻዬ፤

  አንቺ ነሽ

  ውዴ፣ አቻዬ።

  ፍቅርሽ፣ ደግነትሽ

  ገዝቶታል መንፈሴን፤

  ስጦታዬ፣

  ልዩ ነሽ መልካም ሴት።

  ደስ ይለኛል ሳስብ

  እንዳለሽ ከጎኔ፤

  በጥልቅ አክብሮትሽ

  ማርከሽዋል ልቤን።

  (አዝማች)

  ፍቅራችን ይሁን ጽኑ፤

  እንዲህ ተዋደን እንኑር።

  ይሖዋ ይጨመር በትዳራችን

  ውዴ፣ የኔ።

 2. 2. አንተ ነህ ፍቅሬ፣

  የሕይወት አጋሬ፤

  ጓደኛዬ፣

  የምነግርህ ውስጤን።

  ደስታዬ ነው ክብሬ

  ማገልገል አብሬህ፤

  ኩራቴ ነህ ሁሌም፤

  አይታጠፍም ቃሌ።

  (አዝማች)

  ፍቅራችን ይሁን ጽኑ፤

  እንዲህ ተዋደን እንኑር።

  ይሖዋ ይጨመር በትዳራችን

  ውዴ፣ የኔ።

  ፍቅራችን ይሁን ጽኑ፤

  እንዲህ ተዋደን እንኑር።

  ይሖዋ ይጨመር በትዳራችን

  ውዴ፣ የኔ።

  ውዴ፣ የኔ።

  ፍቅሬ።