በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አንድ ሕዝብ ሆነናል

አንድ ሕዝብ ሆነናል

አውርድ፦

 1. 1. የስደት ነፋስ መጥቷል፤

  ደመናው አጥልቷል።

  አይጠፋንም አዝማሚያው፤

  ቀድሞም የምናውቀው ነው።

  ይሖዋ ከኛ ጋር አለ፤

  አንፈራም፣ አንሰጋም።

  የደገኑብን መሣሪያ

  ይከሽፋል፣ አይሳካም።

  (አዝማች)

  አንድ ነን፤ አንድ ሕዝብ ሆነናል፤

  ፍቅር አሰባስቦናል።

  አብረን ነን ምንም ቢመጣ፤

  ይሖዋም ያጸናናል።

  ይሖዋ ያጸናናል።

 2. 2. እስኪደርስልን ፈጥኖ፣

  እስኪታደገን ጌታ፣

  ዓይኖቻችን በተስፋ

  ያያሉ ይሖዋን።

  ሕዝቦቹን መች ትቶ ያውቃል?

  አዎ፣ ያበረታናል።

  ታላቁን አምላክ ይዘናል፤

  ማን ጠላት ይረታናል!

  (አዝማች)

  አንድ ነን፤ አንድ ሕዝብ ሆነናል፤

  ፍቅር አሰባስቦናል።

  አብረን ነን ምንም ቢመጣ፤

  ይሖዋም ያጸናናል።

  (መሸጋገሪያ)

  ማዕበሉ ሲመጣ፣

  እንቆማለን ሳንፈራ።

  ለሕይወታችን አንሳሳም፤

  የይሖዋ ነን እኛ!

  (አዝማች)

  አንድ ነን፤ አንድ ሕዝብ ሆነናል፤

  ፍቅር አሰባስቦናል።

  አብረን ነን ምንም ቢመጣ፤

  ይሖዋም ያጸናናል።

  ይሖዋ ያጸናናል።