በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ውሳኔ

ውሳኔ

አውርድ፦

 1. 1. መላው ጠፍቶኛል፤

  ምን ባደርግ ይሻለኛል?

  ሳላውቀው

  ፍቅር ይዞኝ፣

  ወይኔ ልቤ አታሎኝ።

 2. 2. ሁሌ ትግል

  ላለመውደቅ ስል፣

  ልቤን አልሰማውም ይቅር።

  ቃሉ ይምራኝ ይስጠኝ ምክር።

 3. 3. የሰው ልብ አታላይ፣

  ተንኮለኛ ነው ወላዋይ።

  ሊጥለኝ ነበር አታሎ፤

  አምላክ ባይረዳኝ ኖሮ።

  (አዝማች)

  “በርቺ” ይለኛል፣ “አይዞሽ፤ አልፈልግም ላጣሽ።

  እመኚኝ አለሁ ስልሽ።

  እጄን ያዢ አጥብቀሽ።”

 4. 4. መጥፎ ምርጫ ባደርግ መዘዙ፣

  ቀላል አይደለም ጣጣው ብዙ።

  ውጊያ ላይ ነን ለልባችን ብለን፤

  በንቃት እንጠብቀው።

  የሕይወት ምንጭ ከሱ ነው።

 5. 5. ሳስበው መለስ ብዬ፣

  ’ኮራለሁ በምርጫዬ።

  ቢከብድም፣ ቢያታግልም

  ይሖዋ ትቶኝ አያውቅም።