መኃልየ መኃልይ 6:1-13

  • የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች (1)

  • ልጃገረዷ (2, 3)

    • “እኔ የውዴ ነኝ፤ ውዴም የእኔ ነው” (3)

  • ንጉሡ (4-10)

    • “አንቺ እንደ ቲርጻ ቆንጆ ነሽ” (4)

    • ሴቶቹ የተናገሩትን ጠቀሰ (10)

  • ልጃገረዷ (11, 12)

  • ንጉሡ (እና ሌሎች) (13ሀ)

  • ልጃገረዷ (13ለ)

  • ንጉሡ (እና ሌሎች) (13ሐ)

6  “ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ውድሽ የት ሄደ? ለመሆኑ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው? አብረንሽ እንፈልገው።”   “ውዴ መንጋውን በአትክልት ቦታዎቹ መካከል ለማሰማራትናአበቦችን ለመቅጠፍየቅመማ ቅመም ተክሎች መደብ ወዳለበትወደ አትክልት ቦታው ወርዷል።+   እኔ የውዴ ነኝ፤ውዴም የእኔ ነው።+ እሱ መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።”+   “ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ እንደ ቲርጻ*+ ቆንጆ ነሽ፤+እንደ ኢየሩሳሌምም ውብ ነሽ፤+በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ ታምሪያለሽ።+   ስሜቴን አውከውታልና፣ዓይኖችሽን+ ከእኔ ላይ አንሺ። ፀጉርሽ ከጊልያድ እየተግተለተለ እንደሚወርድየፍየል መንጋ ነው።+   ጥርሶችሽ ታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱየበግ መንጋ ናቸው፤ከመካከላቸውም ግልገሉን ያጣ የለም።   በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።   እርግጥ 60 ንግሥቶች፣80 ቁባቶችናቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ቆነጃጅት ሊኖሩ ይችላሉ።+   እንከን የሌለባት ርግቤ+ ግን አንድ ብቻ ናት። እሷ ለእናቷ ብርቅዬ ልጅ ናት። በወለደቻት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ* ናት። ሴቶች ልጆች አይተዋት ‘የታደልሽ ነሽ’ ይሏታል፤ንግሥቶችና ቁባቶችም ያወድሷታል። 10  ‘እንደ ማለዳ ወጋገን የምታበራ፣*እንደ ሙሉ ጨረቃ ውብ የሆነች፣እንደ ፀሐይ ብርሃን የጠራች፣በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ የምታምረው ይህች ሴት ማን ናት?’”+ 11  “በሸለቆው* ውስጥ ያቆጠቆጡትን ተክሎች ለማየት፣ደግሞም ወይኑ ለምልሞ፣*የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለመመልከትየገውዝ ዛፎች ወዳሉበት ወደ አትክልት ቦታው ወረድኩ።+ 12  ምንም ሳይታወቀኝምኞቴ* የተከበሩ* ወገኖቼየያዟቸው ሠረገሎች ወዳሉበት ወሰደኝ።” 13  “አንቺ ሱላማዊት፣ ተመለሺ፤ ተመለሺ! እናይሽ ዘንድተመለሺ፤ ተመለሺ!” “በሱላማዊቷ ላይ የምታፈጡት ለምንድን ነው?”+ “እሷ የመሃናይምን ጭፈራ* ትመስላለች!”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ውብ ከተማ።”
ወይም “ሰሪሳራዎችሽ።” በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።
ቃል በቃል “የጠራች።”
ቃል በቃል “ወደ ታች የምትመለከት።”
ወይም “በደረቁ ወንዝ።”
ወይም “አቆጥቁጦ።”
ወይም “ነፍሴ።”
ወይም “ፈቃደኛ የሆኑ።”
ወይም “የሁለት ቡድኖች ጭፈራ።”