በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከኖኅ ምን እንማራለን?

አምላክን መታዘዝ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስበህ ታውቃለህ?

• ሥዕሎቹን ተስማሚ ቀለም ቀባ። • ጥቅሶቹን አንብብና አብራራ፤ ከዚያም የተናገሩትን ነገር በክፍት ቦታው ላይ ጻፍ። • እስቲ የሚከተሉትን ነገሮች ከሥዕሎቹ ውስጥ ፈልገህ ለማግኘት ሞክር፦ (1) መሰላል እና (2) የሸረሪት ድር

ኖኅ ለአምላክ ታዛዥ መሆኑ አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ ኤርምያስ 7:23፤ 2 ጴጥሮስ 2:5

ለአምላክ ታዛዥ እንድትሆን ምን ሊረዳህ ይችላል?

ፍንጭ፦ 1 ዜና መዋዕል 28:9፤ ኢሳይያስ 48:17, 18፤ 1 ዮሐንስ 5:3

ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርት አገኘህ?

ምን ይመስልሃል?

አምላክን መታዘዝ እነማንን መታዘዝንም ይጨምራል?

ፍንጭ፦ ኤፌሶን 6:1-3፤ ዕብራውያን 13:7, 17

ካርድ በመሰብሰብ መማር

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ ነህምያ

ጥያቄ

  1. ሀ. ነህምያ ․․․․․ የተባለው የፋርስ ንጉሥ ․․․․․ ሆኖ አገልግሏል።

  2. ለ. ነህምያ የሚለው ስም ትርጉም ምንድን ነው?

  3. ሐ. ነህምያ እንዲህ ብሎ ጸልዮአል፦ “አምላኬ ሆይ ․․․․․”

መልስ

  1. ሀ. አርጤክስስ፣ ጠጅ አሳላፊ።—ነህምያ 1:11፤ 2:1

  2. ለ. “ያህ ያጽናናል።”

  3. ሐ. “. . . በቸርነት አስበኝ።”—ነህምያ 13:31

ሕዝቦችና አገሮች

ታኦንጋ እና መዌልቫን እንባላለን፤ የ6 እና የ8 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በዛምቢያ ነው። በዛምቢያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 90,000፣ 152,000 ወይስ 196,000?

የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከዛምቢያ በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

 

መልስ

  1. መሰላል የሚገኘው በሥዕል 3 ላይ ነው።

  2. የሸረሪት ድር ያለው በሥዕል 2 ላይ ነው።

  3. 152,000