ኢሳይያስ 48:1-22

  • እስራኤል ተወቀሰች፤ ደግሞም ጠራች (1-11)

  • ይሖዋ በባቢሎን ላይ እርምጃ ይወስዳል (12-16ሀ)

  • የአምላክ ትምህርት ጠቃሚ ነው (16ለ-19)

  • “ከባቢሎን ውጡ!” (20-22)

48  እናንተ ራሳችሁን በእስራኤል ስም የምትጠሩ፣+ከይሁዳ ምንጭ የፈለቃችሁ፣*በእውነትና በጽድቅ ባይሆንምበይሖዋ ስም የምትምሉና+የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩየያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ይህን ስሙ።+   እነሱ የቅድስቲቱ ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ ይናገራሉና፤+ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነውንየእስራኤልን አምላክ ድጋፍ ለማግኘት ይጥራሉ።+   “ከብዙ ዘመን በፊት የቀድሞዎቹን* ነገሮች ነግሬአችኋለሁ። ከአፌም ወጥተዋል፤እንዲታወቁም አድርጌአለሁ።+ በድንገት እርምጃ ወሰድኩ፤ እነሱም ተፈጸሙ።+   ምን ያህል ልበ ደንዳና እንደሆንክ፣ይኸውም የአንገትህ ጅማት ብረት፣ ግንባርህም መዳብ መሆኑን ስለማውቅ፣+   ከረጅም ጊዜ በፊት ነግሬሃለሁ። ‘ይህን ያደረገው የራሴ ጣዖት ነው፤ይህን ያዘዘው የተቀረጸው ምስሌና ከብረት የተሠራው ምስሌ* ነው’ እንዳትልገና ከመፈጸሙ በፊት አሳውቄሃለሁ።   አንተም ሰምተሃል፤ ደግሞም ይህን ሁሉ አይተሃል። ይህን አታሳውቅም?*+ ከአሁን ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን፣የማታውቃቸውን ጥብቅ ሚስጥሮች እነግርሃለሁ።+   እነዚህ ነገሮች የተፈጠሩት ጥንት ሳይሆን ገና አሁን ነው፤‘እነዚህንማ ከዚህ በፊት አውቃቸዋለሁ!’ እንዳትል፣ከዛሬ በፊት ሰምተሃቸው አታውቅም።   አዎ፣ አንተ አልሰማህም፤+ አላወቅክምም፤ከዚህ በፊት ጆሮህ ክፍት አልነበረም። በጣም አታላይ እንደሆንክና+ከተወለድክበት ጊዜ ጀምሮ ዓመፀኛ ተብለህ እንደተጠራህ አውቃለሁና።+   ይሁንና ስለ ስሜ ስል ቁጣዬን እቆጣጠራለሁ፤+ስለ ውዳሴዬም ስል ራሴን እገታለሁ፤ደግሞም አላጠፋህም።+ 10  እነሆ፣ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ።+ እንደ ማቅለጫ ምድጃ ባለ መከራ ፈትኜሃለሁ።*+ 11  ለራሴ ስል፣ አዎ ለራሴ ስል እርምጃ እወስዳለሁ፤+ስሜ እንዲረክስ እንዴት እፈቅዳለሁ?+ ክብሬን ለማንም አልሰጥም።* 12  ያዕቆብ ሆይ፣ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማኝ። እኔ ምንጊዜም ያው ነኝ።+ የመጀመሪያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻውም እኔ ነኝ።+ 13  የገዛ እጄ የምድርን መሠረት ጣለ፤+ቀኝ እጄም ሰማያትን ዘረጋ።+ እነሱን ስጠራቸው በአንድነት ይቆማሉ። 14  ሁላችሁም አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ስሙ። ከመካከላቸው እነዚህን ነገሮች ያሳወቀ ማን ነው? ይሖዋ ወዶታል።+ እሱ ደስ የሚያሰኘውን በባቢሎን ላይ ይፈጽማል፤+ክንዱም በከለዳውያን ላይ ያርፋል።+ 15  እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እሱንም ጠርቼዋለሁ።+ አምጥቼዋለሁ፤ መንገዱም የተቃና ይሆናል።+ 16  ወደ እኔ ቅረቡ፤ ደግሞም ይህን ስሙ። ከመጀመሪያው አንስቶ በሚስጥር አልተናገርኩም።+ ከተፈጸመበት ጊዜ አንስቶ እኔ በዚያ ነበርኩ።” አሁንም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ መንፈሱም * ልኮኛል። 17  የሚቤዥህ፣ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦+ “የሚጠቅምህን ነገር* የማስተምርህ፣+ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህእኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+ 18  ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው!+ እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣+ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።+ 19  ዘርህ እንደ አሸዋ፣የአብራክህም ክፋዮች እንደ አሸዋ ቅንጣቶች ብዙ ይሆናሉ።+ ስማቸው ከፊቴ አይጠፋም ወይም አይደመሰስም።” 20  ከባቢሎን ውጡ!+ ከከለዳውያን ሽሹ! ይህን በእልልታ አስታውቁ! አውጁትም!+ እስከ ምድር ዳርቻ እንዲሰማ አድርጉ።+ እንዲህም በሉ፦ “ይሖዋ አገልጋዩን ያዕቆብን ተቤዥቶታል።+ 21  ባድማ በሆኑ ቦታዎች በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም።+ ከዓለት ውስጥ ውኃ አፈለቀላቸው፤ዓለቱን ሰንጥቆ ውኃ አንዶለዶለላቸው።”+ 22  “ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል ይሖዋ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ከይሁዳ ዘር የተገኛችሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “የመጀመሪያዎቹን።”
ወይም “ቀልጦ የተሠራው ሐውልቴ።”
ቃል በቃል “አታሳውቁም?”
ወይም “መርምሬሃለሁ።” “መርጬሃለሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ክብሬን ለማንም አላጋራም።”
ወይም “ከመንፈሱ ጋር።”
ወይም “ለገዛ ጥቅምህ ስል።”