በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 26

ሰዎች ችግርና መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው?

ሰዎች ችግርና መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው?

ሰዎች አሳዛኝ ነገር ሲደርስባቸው “ለምን?” ብለው መጠየቃቸው የተለመደ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የማያሻማ መልስ እንደሚሰጥ ማወቃችን ምንኛ የሚያስደስት ነው!

1. ሰይጣን በዓለም ላይ ለሚታየው መጥፎ ነገር መንስኤ የሆነው እንዴት ነው?

ሰይጣን ዲያብሎስ በአምላክ ላይ ዓምጿል። በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ መግዛት ስለፈለገ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ማለትም አዳምና ሔዋን ከእሱ ጋር አብረው እንዲያምፁ አድርጓል። ሰይጣን ይህን ያደረገው ለሔዋን ውሸት በመንገር ነው። (ዘፍጥረት 3:1-5) ይሖዋ ጥሩ ነገር እንደነፈጋት እንዲሰማት አደረገ። ሰዎች የአምላክን ትእዛዝ ቢጥሱ ይበልጥ ደስተኛ እንደሚሆኑ የሚጠቁም ሐሳብ ሰነዘረ። ሰይጣን ለሔዋን እንደማትሞት በመግለጽ የመጀመሪያውን ውሸት ተናገረ። በዚህም ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣንን “ውሸታምና የውሸት አባት” በማለት ይጠራዋል።—ዮሐንስ 8:44

2. አዳምና ሔዋን ምን ለማድረግ መረጡ?

ይሖዋ ለአዳምና ለሔዋን ብዙ ነገሮችን ሰጥቷቸዋል። ከአንድ ዛፍ በቀር በኤደን ገነት ውስጥ ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ መብላት እንደሚችሉ ነግሯቸው ነበር። (ዘፍጥረት 2:15-17) ያም ሆኖ ግን አዳምና ሔዋን ከዚያ ዛፍ ፍሬ ለመብላት መረጡ። ሔዋን “ከዛፉ ፍሬ ወስዳ በላች።” በኋላ ደግሞ ‘አዳምም በላ።’ (ዘፍጥረት 3:6) ሁለቱም የአምላክን ትእዛዝ ጣሱ። አዳምና ሔዋን ፍጹም ወይም ከኃጢአት ነፃ ስለነበሩ ትክክል የሆነውን ማድረግ ይቀልላቸው ነበር። ሆኖም ሆን ብለው የአምላክን ትእዛዝ በመጣስ ኃጢአት የሠሩ ከመሆኑም ሌላ የእሱን አገዛዝ ለመቀበል አሻፈረኝ አሉ። ይህ ውሳኔ ከባድ መከራ አስከትሎባቸዋል።—ዘፍጥረት 3:16-19

3. አዳምና ሔዋን ያደረጉት ውሳኔ በእኛ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል?

አዳምና ሔዋን ኃጢአት ሲሠሩ ፍጽምና የጎደላቸው ሆኑ፤ ከዚያም ኃጢአትን ለዘሮቻቸው ሁሉ አወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አዳም ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።”ሮም 5:12

ታዲያ መከራ የሚደርስብን ለምንድን ነው? በተለያዩ ምክንያቶች መከራ ሊደርስብን ይችላል። አንዳንዴ እኛ ራሳችን ባደረግነው መጥፎ ውሳኔ ምክንያት ለመከራ ልንዳረግ እንችላለን። ሌሎች ባደረጉት መጥፎ ውሳኔ ምክንያት መከራ የሚደርስብን ጊዜም አለ። ባልተጠበቁ ክስተቶችም ምክንያት መከራ ሊደርስብን ይችላል።—መክብብ 9:11⁠ን አንብብ።

ጠለቅ ያለ ጥናት

አምላክ በዛሬው ጊዜ በዓለም ላይ ለሚታየው ችግርና መከራ ተጠያቂ አይደለም የምንለው ለምን እንደሆነና መከራ ሲደርስብን ምን እንደሚሰማው እንመለከታለን።

4. ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂው ማን ነው?

ብዙ ሰዎች መላውን ዓለም የሚገዛው አምላክ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ይህ እውነት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ

ያዕቆብ 1:13ን እና 1 ዮሐንስ 5:19ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ለሚደርስብን ችግርና መከራ ተጠያቂው አምላክ ነው?

5. የሰይጣን አገዛዝ ምን ውጤት አስከትሏል?

ዘፍጥረት 3:1-6ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ሰይጣን ምን ውሸት ተናግሯል?—ቁጥር 4 እና 5⁠ን ተመልከት።

  • ሰይጣን፣ ይሖዋ የሰው ልጆችን ጥሩ ነገር እንደሚነፍጋቸው የሚጠቁም ምን ሐሳብ ተናግሯል?

  • ሰይጣን፣ ሰዎች ደስተኛ ለመሆን በይሖዋ አገዛዝ ሥር መሆን እንደማያስፈልጋቸው የጠቆመው እንዴት ነው?

መክብብ 8:9ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ምድርን ባልገዛባቸው ጊዜያት በዓለማችን ላይ ምን ነገሮች ተከስተዋል?

  1. ሀ. አዳምና ሔዋን ከኃጢአት ነፃ ነበሩ፤ የሚኖሩትም ገነት ውስጥ ነበር። ሆኖም ሰይጣንን ሰምተው በይሖዋ ላይ ዓመፁ

  2. ለ. በአምላክ ላይ ካመፁ በኋላ ምድራችን በኃጢአት፣ በመከራና በሞት ተሞላች

  3. ሐ. ወደፊት ይሖዋ ኃጢአትን፣ መከራንና ሞትን ያስወግዳል። ሰዎች እንደ ድሮው ከኃጢአት ነፃ ሆነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ

6. ይሖዋ በእኛ ላይ የሚደርሰው መከራ ያሳስበዋል

አምላክ በእኛ ላይ የሚደርሰው መከራ ምንም ግድ አይሰጠውም? ንጉሥ ዳዊትና ሐዋርያው ጴጥሮስ ምን ብለው እንደጻፉ ተመልከት። መዝሙር 31:7ን እና 1 ጴጥሮስ 5:7ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ በእኛ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንደሚመለከትና ሁኔታችን እንደሚያሳስበው ማወቅህ ምን ስሜት ያሳድርብሃል?

7. አምላክ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን መከራ በሙሉ ያስወግዳል

ኢሳይያስ 65:17ን እና ራእይ 21:3, 4ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ በሰው ልጆች ላይ የደረሱት መጥፎ ነገሮች ያስከተሉትን ጉዳት ሙሉ በሙሉ እንደሚያስተካክል ማወቅህ የሚያጽናናህ ለምንድን ነው?

ይህን ታውቅ ነበር?

ሰይጣን የመጀመሪያውን ውሸት ሲናገር የይሖዋን ስም አጥፍቷል። ይሖዋ ፍትሐዊና አፍቃሪ ገዢ እንዳልሆነ የሚያስመስል ሐሳብ በመሰንዘር ስሙን አጉድፏል። በቅርቡ ይሖዋ በሰው ልጆች ላይ የደረሰውን ጉዳት ሙሉ በሙሉ በማስተካከል መልካም ስሙን ያድሳል። በሌላ አባባል የእሱ አገዛዝ ከሁሉ የተሻለ እንደሆነ ያሳያል። የይሖዋ ስም መቀደስ ወይም ከነቀፋ ነፃ መሆን በጽንፈ ዓለም ውስጥ ተቀዳሚ ቦታ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።—ማቴዎስ 6:9, 10

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “የተፈጠርነው ለመከራ ነው።”

  • አንተ ምን ትላለህ?

ማጠቃለያ

በዓለም ላይ ለሚታየው መጥፎ ነገር በዋነኝነት ተጠያቂ የሆኑት ሰይጣን ዲያብሎስና የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ናቸው። ይሖዋ የሚደርስብን መከራ በጣም ያሳስበዋል፤ በቅርቡ ደግሞ የደረሰብንን ጉዳት በሙሉ ያስተካክላል።

ክለሳ

  • ሰይጣን ዲያብሎስ ለሔዋን ምን ውሸት ነግሯታል?

  • የአዳምና የሔዋን ዓመፅ በእኛ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል?

  • ይሖዋ የሚደርስብን መከራ እንደሚያሳስበው በምን እናውቃለን?

ግብ

ምርምር አድርግ

ኃጢአት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ይሰጣል?

“ኃጢአት ምንድን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

ሰይጣን ዲያብሎስ በኤደን ገነት ስላስነሳው አወዛጋቢ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ርዕስ አንብብ።

“አምላክ መከራና ሥቃይ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?” (መጠበቂያ ግንብ ጥር 1, 2014)

አንድ ሰው በዙሪያው የሚያየውን ችግር በተመለከተ ምን ተገንዝቧል?

ከአሁን በኋላ ብቻዬን አይደለሁም (5:09)