በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 1 ክለሳ

ክፍል 1 ክለሳ

ከአስተማሪህ ጋር በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  1. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ከሚሰጣቸው ተስፋዎች መካከል ትኩረትህን የሚስበው የትኛው ነው?

    (ምዕራፍ 02 ተመልከት።)

  2. መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ብለህ እንድታምን ያደረገህ ምንድን ነው?

    (ምዕራፍ 03ን እና 05 ተመልከት።)

  3. ይሖዋ የሚለውን የአምላክ ስም መጠቀም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

    (ምዕራፍ 04 ተመልከት።)

  4. መጽሐፍ ቅዱስ “የሕይወት ምንጭ” አምላክ እንደሆነ ይናገራል። (መዝሙር 36:9) በዚህ ታምናለህ?

    (ምዕራፍ 06 ተመልከት።)

  5. ምሳሌ 3:32ን አንብቡ።

    •   ይሖዋ ከማንም የተሻለ ወዳጅ ይሆነናል የምንለው ለምንድን ነው?

    •   ይሖዋ ከወዳጆቹ ምን ይጠብቃል? እነዚህን ነገሮች የሚጠብቅ መሆኑ ምክንያታዊ ይመስልሃል?

      (ምዕራፍ 07ን እና 08 ተመልከት።)

  6. መዝሙር 62:8ን አንብቡ።

    •   ወደ ይሖዋ የጸለይክባቸው አንዳንድ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? ሌላስ ስለ ምን ነገር ልትጸልይ ትችላለህ?

    •   ይሖዋ ለጸሎታችን መልስ የሚሰጠው እንዴት ነው?

      (ምዕራፍ 09 ተመልከት።)

  7. ዕብራውያን 10:24, 25ን አንብቡ።

    •   በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘትህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

    •   በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት የምትከፍለው መሥዋዕትነት የሚያስቆጭ ይመስልሃል?

      (ምዕራፍ 10 ተመልከት።)

  8. መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረህ ማንበብህ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን የምታነብበት ፕሮግራም አለህ? ካለህ ለዚህ የመደብከው የትኛውን ሰዓት ነው?

    (ምዕራፍ 11 ተመልከት።)

  9. እስካሁን ካደረግነው የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት በጣም ያስደሰተህ የትኛው ነው?

  10. መጽሐፍ ቅዱስን መማር ከጀመርክ ወዲህ ምን ተፈታታኝ ሁኔታ አጋጥሞሃል? መማርህን እንድትቀጥል የሚረዳህ ምንድን ነው?

    (ምዕራፍ 12 ተመልከት።)