በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ ምን ይመስላል?

የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ ምን ይመስላል?

 መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው?

 መጽሐፍ ቅዱስን ርዕስ በርዕስ የሚያስተምርህ አስተማሪ ይመደብልሃል። ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ በመጠቀም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኘው ሐሳብ እንዲሁም መልእክቱ አንተን የሚጠቅምህ እንዴት እንደሆነ ደረጃ በደረጃ ትማራለህ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ቪዲዮ ተመልከት።

 ለትምህርቱ ክፍያ እጠየቃለሁ?

 በፍጹም። የይሖዋ ምሥክሮች፣ ኢየሱስ “በነፃ እንደተቀበላችሁ በነፃ ስጡ” በማለት ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠውን መመሪያ ይከተላሉ። (ማቴዎስ 10:8) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ እና ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ ጨምሮ ለኮርሱ ለሚያስፈልጉት ነገሮች ክፍያ አይጠይቁም።

 ኮርሱ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

 ሙሉው ኮርስ 60 ምዕራፎች የያዘ ነው። ትምህርቱ የሚወስደው ጊዜ በአንተ ላይ የተመካ ነው፤ ሆኖም ብዙ ተማሪዎች በሳምንት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ምዕራፍ ያጠናሉ።

 ትምህርቱን የምጀምረው እንዴት ነው?

  1.  1. ኢንተርኔት ላይ የሚገኘውን ቅጽ ሙላ። ቅጹ ላይ የሞላኸውን የግል መረጃ የምንጠቀምበት አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ያቀረብከውን ጥያቄ ለማስተናገድ ብቻ ነው።

  2.  2. አንድ አስተማሪ በአድራሻህ ተጠቅሞ ያነጋግርሃል። አስተማሪህ፣ አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሱ ምን እንደሚመስል ያብራራልሃል፤ ጥያቄዎች ካሉህም መልስ ይሰጥሃል።

  3.  3. አንተና አስተማሪህ ተነጋግራችሁ የምታጠናበትን ፕሮግራም ታመቻቻላችሁ። ትምህርቱን በአካል በመገናኘት ወይም በስልክ፣ በቪዲዮ፣ በደብዳቤ ወይም በኢሜይል አማካኝነት ማካሄድ ይቻላል። የትምህርት ክፍለ ጊዜው በአብዛኛው አንድ ሰዓት ያህል ቢወስድ ነው፤ ሆኖም ከፕሮግራምህ ጋር በሚስማማ መልኩ ማሳጠርም ማስረዘምም ይቻላል።

 ትምህርቱ ይሆነኝ እንደሆነና እንዳልሆነ አስቀድሜ መሞከር እችላለሁ?

 አዎ። መጀመሪያ ኢንተርኔት ላይ የሚገኘውን ቅጽ ሙላ። የተመደበልህ አስተማሪ በአድራሻህ ተጠቅሞ ሲያነጋግርህ፣ በቅድሚያ ኮርሱን ትወደው እንደሆነና እንዳልሆነ መሞከር እንደምትፈልግ ንገረው። እሱም ሦስት ምዕራፎችን ብቻ የያዘውን ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ ትምህርቱን ያስጀምርሃል፤ ይህም ኮርሱን ትወደው እንደሆነና እንዳልሆነ ለማየት አጋጣሚ ይሰጥሃል።

 የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቱን ብጀምር የይሖዋ ምሥክር እንድሆን ይጠበቅብኛል?

 አይጠበቅብህም። የይሖዋ ምሥክሮች ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር ያስደስታቸዋል፤ ሆኖም ማንም ሰው እምነታቸውን እንዲቀበል ጫና አያደርጉም። ለሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ስናስተምር አመለካከታቸውን እናከብራለን፤ እያንዳንዱ ግለሰብ የፈለገውን መርጦ የማመን መብት እንዳለው እንገነዘባለን።—1 ጴጥሮስ 3:15

 የራሴን መጽሐፍ ቅዱስ መጠቀም እችላለሁ?

 አዎ፣ የፈለግከውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መጠቀም ትችላለህ። እኛ የምንመርጠው፣ ግልጽና ትክክለኛ የሆነውን አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም ብዙ ሰዎች የለመዱትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መጠቀም እንደሚመርጡ እንገነዘባለን።

 ሌሎችም አብረውኝ እንዲማሩ መጋበዝ እችላለሁ?

 አዎ። ከፈለግክ ቤተሰብህን በሙሉ ወይም ጓደኞችህን መጋበዝ ትችላለህ።

 ከዚህ በፊት ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን አጠና ከነበረስ? እንደገና ትምህርቱን መጀመር እችላለሁ?

 አዎ። እንዲያውም አሁን የምንሰጠውን ኮርስ ከበፊቱ የበለጠ እንደምትወደው እንተማመናለን፤ ምክንያቱም በዛሬው ጊዜ ሰዎች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግምት ውስጥ በማስገባት የተዘጋጀ ኮርስ ነው። በፊት ከነበሩን ኮርሶች የበለጠ ብዙ ቪዲዮዎች ያካተተና አሳታፊ ነው።

 ያለአስተማሪ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት የሚቻልበት ዝግጅት አላችሁ?

 አዎ። እርግጥ ነው፣ አብዛኞቹ ተማሪዎች የተሻለ ጥቅም የሚያገኙት በአስተማሪ እገዛ ሲያጠኑ ነው፤ ያም ቢሆን አንዳንዶች መጀመሪያ ላይ ያለአስተማሪ እገዛ በራሳቸው ቢያጠኑ ይመርጣሉ። አንተም ምርጫህ ይህ ከሆነ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ መሣሪያዎች በተባለው ገጽ ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠና የሚያግዙህ መጻሕፍትና ሌሎች መሣሪያዎች በነፃ ማግኘት ትችላለህ። ለምሳሌ የሚከተሉት ጠቃሚ መሣሪያዎች ተዘጋጅተውልሃል፦