በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የቪዲዮ ትምህርቶች

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ቪዲዮዎች—መሠረታዊ ትምህርቶች

እነዚህ አጫጭር ቪዲዮዎች መሠረታዊ ለሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ ሲሆኑ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! በተባለው ብሮሹር ላይ የተመሠረቱ ናቸው።

 

ከአምላክ የተላከ ምሥራች!

ከአምላክ የመጣው ምሥራች ምንድን ነው? በዚሀ ምሥራች ማመን የሚኖርብንስ ለምንድን ነው? ይህ ብሮሹር ለተለመዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

አምላክ ስም አለው?

አምላክ ብዙ የማዕረግ ስሞች አሉት፤ ከእነዚህ ስሞች መካከል ሁሉን ቻይ፣ ፈጣሪ እና ጌታ የሚሉት ይገኙበታል። ይሁንና የአምላክ የግል ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ 7,000 ጊዜ ይገኛል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ከሆኑ የአምላክ ቃል ሊባል ይችላል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የማን ሐሳብ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈው አምላክ ከሆነ እስከ ዛሬ ከተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ የላቀ መሆን አለበት።

ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ሞት ለሰው ልጆች ከፍተኛ ጥቅም እንዳስገኘ ይናገራል። ለመሆኑ የኢየሱስ ሞት ምን ጥቅም አስገኝቷል?

አምላክ ምድርን የፈጠረው ለምንድን ነው?

ምድራችን በሚያስደምሙ ውብ ነገሮች የተሞላች ናት። ከፀሐይ ያላት ርቀት፣ ያጋደለችበት መጠን እንዲሁም በዛቢያዋ ላይ የምትሽከረከርበት ፍጥነት የተስተካከለ ነው። ለመሆኑ አምላክ ይህን ያህል ተጠቦ ምድራችንን የፈጠረበት ዓላማ ምንድን ነው?

ስንሞት ምን እንሆናለን?

መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ሰዎች እንደ አልዓዛር ትንሣኤ የሚያገኙበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል።

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ከየትኛውም ርዕሰ ጉዳይ ይበልጥ ያስተማረው ስለ አምላክ መንግሥት ነው። ለበርካታ መቶ ዘመናት፣ የኢየሱስ ተከታዮች ይህ መንግሥት እንዲመጣ ሲጸልዩ ኖረዋል።