በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 48

ጓደኞችህን በጥበብ ምረጥ

ጓደኞችህን በጥበብ ምረጥ

ጥሩ ጓደኞች በደስታችን ጊዜ አብረውን ይደሰታሉ፤ ችግር ሲያጋጥመን ደግሞ እንድንበረታ ይረዱናል። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መመሥረት ጉዳት ሊኖረው እንደሚችል ያስጠነቅቃል። ታዲያ ጥሩ ጓደኞችን መምረጥ የምትችለው እንዴት ነው? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ተመልከት።

1. የምትመርጣቸው ጓደኞች በአንተ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ?

ሁላችንም ብንሆን አብረውን ጊዜ የሚያሳልፉ ሰዎችን የመምሰል ዝንባሌ አለን። ይህ ጥቅምም ጉዳትም ሊኖረው ይችላል፤ አብረን ጊዜ የምናሳልፈው በአካልም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት መሆኑ በዚህ ረገድ ለውጥ አያመጣም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው “ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል፤ ከሞኞች [ይሖዋን ከማይወዱ ሰዎች] ጋር የሚገጥም ግን ጉዳት ይደርስበታል።” (ምሳሌ 13:20) ይሖዋን የሚወዱና የሚያመልኩ ጓደኞች ከይሖዋ ጋር ተቀራርበህ እንድትኖርና ጥሩ ውሳኔ እንድታደርግ ይረዱሃል። ይሖዋን የማይወዱ ጓደኞች ግን ከእሱ እንድትርቅ ሊያደርጉህ ይችላሉ። በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ ጓደኞቻችንን በጥበብ እንድንመርጥ የሚያበረታታን መሆኑ አያስገርምም! አምላክን ከሚወዱ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መመሥረታችን እኛንም ሆነ እነሱን ይጠቅማል። ‘እርስ በርስ ለመበረታታት እንዲሁም ለመተናነጽ’ ያስችለናል።—1 ተሰሎንቄ 5:11

2. ይሖዋ የምትመርጣቸውን ጓደኞች ሲያይ ምን ይሰማዋል?

ይሖዋ ጓደኞቹን የሚመርጠው በጥበብ ነው። “የጠበቀ ወዳጅነት” የሚመሠርተው “ከቅኖች ጋር” ነው። (ምሳሌ 3:32) ይሖዋ እሱን ከማይወዱ ሰዎች ጋር ጓደኝነት ስንመሠርት ምን ይሰማዋል? በጣም እንደሚያዝን የታወቀ ነው! (ያዕቆብ 4:4⁠ን አንብብ።) በሌላ በኩል ግን ከመጥፎ ጓደኞች የምንርቅ እንዲሁም ወደ ይሖዋና እሱን ወደሚወዱ ሰዎች የምንቀርብ ከሆነ ይሖዋ ይደሰታል፤ በተጨማሪም ከእኛ ጋር ወዳጅነት ይመሠርታል።—መዝሙር 15:1-4

ጠለቅ ያለ ጥናት

ጥሩ ጓደኞችን መምረጥህ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነና በሕይወትህ ላይ በጎ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጓደኞችን ማግኘት የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

3. ከመጥፎ ጓደኞች ራቅ

መጥፎ ጓደኞች የሚባሉት አምላክንና የእሱን መሥፈርቶች የማይወዱ ሰዎች ናቸው። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ሳይታወቀን ከመጥፎ ጓደኞች ጋር ልንገጥም የምንችለው እንዴት ነው?

አንደኛ ቆሮንቶስ 15:33ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • መጥፎ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው? ለምን?

መዝሙር 119:63ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ጓደኛ ስትመርጥ መመዘኛህ ሊሆን የሚገባው ምንድን ነው?

አንድ የተበላሸ ፍሬ ሌሎቹን ፍሬዎች ሁሉ ሊያበላሽ ይችላል። አንድ መጥፎ ጓደኛስ በአንተ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችለው እንዴት ነው?

4. ከእኛ በጣም የተለዩ ሰዎች ጥሩ ጓደኛ ሊሆኑን ይችላሉ

መጽሐፍ ቅዱስ በጥንቷ እስራኤል ስለኖሩ ዳዊትና ዮናታን የተባሉ ሰዎች ይናገራል። ሁለቱ ሰዎች ዕድሜያቸውም ሆነ አስተዳደጋቸው ፈጽሞ የተለያየ ነው፤ ሆኖም በጣም የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረት ችለዋል። አንደኛ ሳሙኤል 18:1ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ጓደኛ አድርገን የምንመርጣቸው ሰዎች የግድ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ዕድሜ ወይም የኑሮ ደረጃ ሊኖራቸው የማይገባው ለምንድን ነው?

ሮም 1:11, 12ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋን የሚወዱ ጓደኛሞች እርስ በርስ ሊበረታቱ የሚችሉት እንዴት ነው?

በቀጣዩ ቪዲዮ ላይ አንድ ወጣት ወንድም ባላሰበው ቦታ ጓደኛ ያገኘው እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ የአኪል ወላጆች የልጃቸው የትምህርት ቤት ጓደኞች ጉዳይ ያሳሰባቸው ለምንድን ነው?

  • መጀመሪያ ላይ አኪል ከእነዚህ ልጆች ጋር ጓደኛ መሆን የፈለገው ለምን ነበር?

  • የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፍ የቻለው እንዴት ነው?

5. ጥሩ ጓደኞች ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ጥሩ ጓደኞች ማግኘትና አንተም ለሌሎች ጥሩ ጓደኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ

ምሳሌ 18:24ን እና 27:17ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • እውነተኛ ጓደኞች እርስ በርስ የሚረዳዱት እንዴት ነው?

  • አንተስ እንዲህ ዓይነት ጥሩ ጓደኞች አሉህ? ከሌሉህ እንዲህ ዓይነት ጓደኞች ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ፊልጵስዩስ 2:4ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ጥሩ ጓደኛ ለማግኘት አንተ ራስህ ጥሩ ጓደኛ መሆን አለብህ። እንዲህ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

ጥሩ ጓደኞች ለማግኘት አንተ ራስህ ጥሩ ጓደኛ መሆን አለብህ

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ጥሩ ያልሆነ ጓደኛም ቢሆን ከምንም ይሻላል።”

  • አንተ ምን ትላለህ?

ማጠቃለያ

ጓደኞቻችንን በጥበብ መምረጣችን ይሖዋን የሚያስደስተው ከመሆኑም ሌላ እኛንም ይጠቅመናል።

ክለሳ

  • ይሖዋ ጥሩ ጓደኞች እንድንመርጥ የሚፈልገው ለምንድን ነው?

  • ከምን ዓይነት ጓደኞች መራቅ ይኖርብናል?

  • በጎ ተጽዕኖ ሊያሳድሩብህ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ጠንካራ ወዳጅነት መመሥረት የምትችለው እንዴት ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ጥሩ ጓደኞች በችግር ጊዜ ሊረዱን የሚችሉት እንዴት ነው?

“መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት ወዳጅነታችሁን አጠናክሩ” (መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 2019)

በኢንተርኔት አማካኝነት ጓደኝነት ስለመመሥረት ልታውቃቸው የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው?

ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን (4:12)

“የአባት ፍቅር ለማግኘት በጣም እመኝ ነበር” የሚል ርዕስ ባለው የሕይወት ታሪክ ላይ አንድ ሰው የጓደኛ ምርጫውን መለስ ብሎ እንዲገመግም ያነሳሳው ምንድን ነው?

“መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል” (መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1, 2012)