በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ሞትን ከመፍራት ነፃ መውጣት የምትችለው እንዴት ነው?

ሞትን ከመፍራት ነፃ መውጣት የምትችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሞትን እንደ ጠላታችን በመመልከት ተገቢ በሆነ መንገድ የምንፈራው ከሆነ ሕይወታችን አደጋ ላይ እንዳይወድቅ አንዳንድ እርምጃዎችን እንወስዳለን። (1 ቆሮንቶስ 15:26) ያም ቢሆን በሐሰት ትምህርቶችና በአጉል እምነት ምክንያት የሚመጣ መሠረተ ቢስ የሞት ፍርሃት ሰዎች “በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ ለባርነት [እንዲዳረጉ]” ምክንያት ሆኗል። (ዕብራውያን 2:15) ሞትን መፍራት በሕይወትህ ደስታ እንዳታገኝ እንቅፋት ይሆንብሃል፤ እውነትን ማወቅ ግን ለሞት ከልክ ያለፈ ፍርሃት እንዳያድርብህ በመከላከል ነፃ ያወጣሃል።ዮሐንስ 8:32

ስለ ሞት እውነታው ምንድን ነው?

  • የሞቱ ሰዎች ከሕልውና ውጪ ናቸው። (መዝሙር 146:4) መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን ከእንቅልፍ ጋር ስለሚያመሳስለው ከሞትኩ በኋላ ልሠቃይ አችላለሁ ብለህ ልትፈራ አይገባም።መዝሙር 13:3፤ ዮሐንስ 11:11-14

  • ሙታን ጉዳት ሊያደርሱብን አይችሉም። ቀደም ሲል ጉዳት ያደርሱብን የነበሩ ጠላቶቻችን እንኳ ከሞቱ በኋላ “መንፈሳቸው ተነሥቶ አይመጣም።” (ኢሳይያስ 26:14) መጽሐፍ ቅዱስ ‘ጥላቻቸውና ቅናታቸው ከጠፋ ቆይቷል’ ይላል።መክብብ 9:6

  • እርግጥ ስንሞት ሕልውናችን እስከ መጨረሻው ያከትማል ማለት አይደለም። አምላክ በትንሣኤ አማካኝነት የሞቱ ሰዎችን መልሶ ሕያው ያደርጋቸዋል።ዮሐንስ 5:28, 29፤ የሐዋርያት ሥራ 24:15

  • አምላክ ‘ሞት የማይኖርበት’ ጊዜ እንደሚመጣ ቃል ገብቷል። (ራእይ 21:4) መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ጊዜ አስመልክቶ ሲናገር “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእርሷም ለዘላለም ይኖራሉ” ይላል። በዚህ ወቅት የሚኖሩ ሰዎች ከማንኛውም ዓይነት የሞት ፍርሃት ሙሉ በሙሉ ነፃ ይወጣሉ።መዝሙር 37:29