በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ሐዋርያው ጳውሎስ የቀረበበት ‘የፍርድ ወንበር’ ምንድን ነው?

በ⁠የሐዋርያት ሥራ 18:12, 13 ላይ የሚገኘው ዘገባ እንደሚናገረው በቆሮንቶስ የሚገኙ አይሁዳውያን፣ ጳውሎስን ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ የሌሎችን እምነት እያስቀየረ እንደሆነ በመወንጀል “በፍርድ ወንበር” ወይም ቪማ (በግሪክኛ “መድረክ” ማለት ነው) ፊት አቅርበውት ነበር። በጥንቷ ቆሮንቶስ በገበያ ስፍራው መሃል አካባቢ ከፍ ያለ ቦታ ላይ የሚገኝ መድረክ ነበር፤ ይህ ቦታ የሚገኘው በምኩራቡ አቅራቢያ ይመስላል። መድረኩ የነበረበት ቦታ ለሕዝቡ ንግግር ለመስጠት አመቺ ነበር። ተናጋሪው የሚቆምበት መድረክ በሰማያዊና በነጭ እብነ በረድ የተሠራና በሚያማምሩ ቅርጾች ያጌጠ ነው። መድረኩ ላይ ሁለት መቆያ ክፍሎች አሉ፤ በክፍሎቹ ውስጥ የሚገኙት ወንበሮች የተሠሩት በእብነ በረድ ሲሆን ወለሉ ደግሞ በጠጠር በተሠሩ ሥዕሎች ያጌጠ ነበር።

ሐዋርያው ጳውሎስ የቀረበበት የፍርድ ወንበር ይህ መድረክ ሳይሆን አይቀርም፤ ጳውሎስ የአካይያ አገረ ገዥ በነበረው በሮማዊው በጋልዮስ ፊት ቀርቦ ነበር። በዚህ ቦታ ላይ የሚቀመጡ ባለሥልጣናት የፍርድ ጉዳዮችን ይሰሙ እንዲሁም ውሳኔዎችን ለተሰበሰበው ሕዝብ ያስታውቁ ነበር።

በግሪክ ከተሞች ውስጥ ሕዝቡ እንዲህ ባለው ቪማ ፊት መሰብሰባቸው የተለመደ ነበር፤ በዚህ ቦታ ላይ ማንኛውም ዓይነት ሕዝባዊ ጉዳይ ይፈጸማል። ስለ ኢየሱስ የፍርድ ሂደት በሚናገረው ዘገባ ላይ በ⁠ማቴዎስ 27:19 እና በ⁠ዮሐንስ 19:13 ላይ የሚገኘው የግሪክኛ ጥቅስ፣ ጳንጥዮስ ጲላጦስ ሕዝቡን ያነጋገረው ከቪማው ላይ እንደሆነ ይገልጻል።—ከየሐዋርያት ሥራ 12:21 ጋር አወዳድር።

ኢየሱስ የተገደለበት መንገድ ለአንዳንድ አይሁዳውያን መሰናክል የሆነባቸው ለምንድን ነው?

ሐዋርያው ጳውሎስ የጥንቶቹን ክርስቲያኖች አስመልክቶ ሲናገር “እኛ . . . የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁዳውያን መሰናክል ለአሕዛብ ደግሞ ሞኝነት ነው” ብሏል። (1 ቆሮንቶስ 1:23) ኢየሱስ የተገደለበት መንገድ አንዳንዶች እንዲሰናከሉ ምክንያት የሆነው ለምንድን ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ የሆኑት ቤን ዊዘሪንግተን ሣልሳዊ፣ ኢየሱስ ስለተገደለበት መንገድና በመጀመሪያው መቶ ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ሰዎች ስለነበራቸው ባሕል ጽፈዋል፤ እኚህ ሰው ኢየሱስ የተገደለበት መንገድ “በዚያ ዘመን እጅግ አሳፋሪ” እንደነበርና አሟሟቱም “ክብር ባለው መንገድ ሰማዕት እንደመሆን ተደርጎ [እንዳልተቆጠረ]” ገልጸዋል። ዊዘሪንግተን አክለውም እንዲህ ብለዋል፦ “በዚያ ዘመን የነበሩ ሰዎች አንድ ሰው የሚሞትበት መንገድ ስለ ማንነቱ እንደሚገልጽ ያምኑ ነበር። ከዚህ አንጻር ኢየሱስ አጭበርባሪና አገር የከዳ እንዲሁም ዓመፀኛ ባሪያዎች በሚቀጡበት መንገድ መቀጣት የሚገባው ሰው እንደሆነ ተደርጎ ተቆጥሮ ነበር።” የጥንቶቹ ክርስቲያኖች እንዲህ ባለው ባሕል ውስጥ የነበሩ እንደመሆናቸው መጠን ስለ ኢየሱስ ሞት እና ትንሣኤ የሚናገሩትን ዘገባዎች ፈጥረው እንደጻፉት ማሰቡ ምክንያታዊ አይሆንም።