ኢየሱስ ለፖለቲካ ምን አመለካከት ነበረው?
ኢየሱስ ለፖለቲካ ምን አመለካከት ነበረው?
ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ እንዲገባ በተለያዩ ወቅቶች ጫና ተደርጎበት እንደነበረ የወንጌል ጸሐፊዎች ዘግበዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ ከተጠመቀ ብዙም ሳይቆይ የዓለም ገዥ እንዲሆን ዲያብሎስ ግብዣ አቅርቦለት ነበር። ቆየት ብሎም አገልግሎቱን በሚያከናውንበት ወቅት ሕዝቡ ንጉሥ ሊያደርጉት ፈልገው ነበር። ከጊዜ በኋላ ደግሞ አንዳንዶች የፖለቲካዊ ንቅናቄ አራማጅ እንዲሆን ጫና አድርገውበታል። ታዲያ ኢየሱስ በእነዚህ ወቅቶች ምን አደረገ? እስቲ እነዚህን ዘገባዎች አንድ በአንድ እንመልከት።
የዓለም ገዥ፦ የወንጌል ዘገባዎች እንደሚገልጹት ኢየሱስ “የዓለምን መንግሥታት ሁሉ” እንዲገዛ ዲያብሎስ ግብዣ አቅርቦለት ነበር። ኢየሱስ ይህን ግብዣ ቢቀበል ኖሮ የሰው ዘርን ችግሮች በማስወገድ ረገድ ምን ያህል ሊሳካለት ይችል እንደነበር አስበው! የሰው ልጆች እድገት ከልቡ የሚያሳስበው ማንኛውም ፖለቲከኛ እንዲህ ዓይነት ግብዣ ቢቀርብለት ዓይኑን ሳያሽ እንደሚቀበል ጥርጥር የለውም። ኢየሱስ ግን ይህን ግብዣ ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበረም።—ማቴዎስ 4:8-11
ንጉሥ፦ ኢየሱስ በኖረበት ዘመን የነበሩት አብዛኞቹ አይሁዳውያን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ችግሮቻቸውን የሚፈታ መሪ አጥብቀው ይሹ ነበር። ሕዝቡ፣ ኢየሱስ በነበረው ችሎታ በጣም ስለተደነቁ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ እንዲገባ ለማድረግ ፈልገው ነበር። ታዲያ እሱ ምን ምላሽ ሰጠ? የወንጌል ጸሐፊው ዮሐንስ እንደዘገበው “ኢየሱስ መጥተው ሊይዙትና ሊያነግሡት እንዳሰቡ ስላወቀ ብቻውን ዳግመኛ ወደ ተራራ ገለል አለ።” (ዮሐንስ 6:10-15) በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ኢየሱስ በፖለቲካ ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ አልሆነም።
የፖለቲካዊ ንቅናቄ አራማጅ፦ ኢየሱስ ከመገደሉ ከጥቂት ቀናት በፊት ምን እንደተከናወነ እስቲ እንመልከት። ከሮም አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚፈልጉት የፈሪሳውያን ተከታዮች እና የሄሮድስን ሥርወ መንግሥት የሚደግፉት የሮም አገዛዝ አቀንቃኞች ወደ ኢየሱስ መጡ። እነዚህ ሰዎች በፖለቲካው ረገድ ከአንዱ ወገን እንዲቆም በኢየሱስ ላይ ጫና ለማሳደር ፈልገው ነበር። በመሆኑም አይሁዳውያን ለሮም ግብር መክፈል ይኖርባቸው እንደሆነ ጠየቁት።
የማርቆስ ዘገባ ኢየሱስ ምን ምላሽ እንደሰጠ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “‘ለምን ትፈትኑኛላችሁ? እስቲ አንድ ዲናር ማርቆስ 12:13-17) ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት—የሁለት አገዛዞች ታሪክ (እንግሊዝኛ) የተባለው መጽሐፍ ኢየሱስ ይህን ምላሽ የሰጠበትን ምክንያት አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦ “ፖለቲካዊ መሲሕ ለመሆን ፈቃደኛ ያልነበረ ከመሆኑም ሌላ ለቄሳር መስጠት ያለብንና ለአምላክ መስጠት ያለብን ምን እንደሆነ በግልጽ ጠቁሟል።”
አምጡና አሳዩኝ’ አላቸው። እነሱም አመጡለት። እሱም ‘ይህ ምስልና የተቀረጸው ጽሑፍ የማን ነው?’ አላቸው። እነሱም ‘የቄሳር’ አሉት። ከዚያም ኢየሱስ ‘የቄሳር የሆነውን ነገር ለቄሳር የአምላክ የሆነውን ነገር ደግሞ ለአምላክ መልሳችሁ ስጡ’ አላቸው።” (ክርስቶስ እንዲህ ያለ አቋም የወሰደው በወቅቱ የነበሩት እንደ ድህነት፣ ሙስና እና የፍትሕ መጓደል ያሉ ችግሮች ግድ ስለማይሰጡት አልነበረም። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያሳየው ሕዝቡ የነበረበት አሳዛኝ ሁኔታ የኢየሱስን ስሜት በጥልቅ ነክቶት ነበር። (ማርቆስ 6:33, 34) ከዚህም ሌላ አንዳንዶች በወቅቱ በነበሩት አወዛጋቢ ሁኔታዎች ውስጥ እጁን እንዲያስገባ ለማነሳሳት ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ ነበር፤ ያም ቢሆን ኢየሱስ በዓለም ላይ ያለውን የፍትሕ መጓደል ለማስወገድ ዘመቻ አላካሄደም።
እነዚህ ዘገባዎች በግልጽ እንደሚያሳዩት ኢየሱስ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ አልነበረም። ታዲያ በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችስ ምን ሊያደርጉ ይገባል?