በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ድህነት የሚያከትምበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ድህነት የሚያከትምበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ድህነት የሚያከትምበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

የጥንቷ እስራኤል ንጉሥ የነበረው ጠቢቡ ሰሎሞን “እነሆም፣ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፣ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም” በማለት ተናግሯል። (መክብብ 4:1) ሰሎሞን እንዲህ ብሎ ከተናገረላቸው የተጨቆኑ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በድህነት የሚማቅቁ እንደነበሩ አያጠራጥርም።

ድህነት የሚለካው አንድ ሰው በሚያገኘው የገንዘብ መጠን ብቻ አይደለም። የዓለም ባንክ በሰኔ 2002 ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው “በ1998 በዓለም ዙሪያ 1.2 ቢልዮን የሚያህሉ ሰዎች ከ1 ዶላር በሚያንስ የዕለት ገቢ ይተዳደሩ እንደነበር የሚገመት ሲሆን ከ2 ዶላር የሚያንስ የዕለት ገቢ የነበራቸው ደግሞ 2.8 ቢልዮን ይሆናሉ።” የሰዎቹ ቁጥር ቀደም ሲል ከተገመተው የሚያንስ ቢሆንም “የሰው ልጅ በድህነት ሳቢያ ከሚደርስበት መከራ አንጻር ሲታይ ግን አሁንም በጣም የከፋ ችግር እንዳለ የሚጠቁም ነው።

ድህነት የሚያከትምበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ “ድሆችስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና” ብሏቸው ነበር። (ዮሐንስ 12:8) ይህ ሲባል ግን ድህነትና ከድህነት ጋር የተያያዙ ችግሮች ለዘላለም ይቀጥላሉ ማለት ነውን? በፍጹም፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሃብታም እንደሚሆኑ ቃል ባይገባላቸውም ከእነዚህ ቃላት በመነሳት ድሆች ከችግራቸው የሚላቀቁበት ምንም ተስፋ የላቸውም ብለን መደምደም አይኖርብንም።

የሰው ልጆች ድህነትን ለማስቀረት የሰጧቸው ተስፋዎችና ያደረጓቸው ጥረቶች ቢከሽፉም የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ በቅርቡ ድህነት እንደሚወገድ ማረጋገጫ ይሰጠናል። እንዲያውም ኢየሱስ “ለድሆች ወንጌልን” ሰብኳል። (ሉቃስ 4:18) ይህ ወንጌል ድህነት እንደሚወገድ የተሰጠውን ተስፋ ጨምሮ ይዟል። ይህ ተስፋ የአምላክ መንግሥት በምድር ላይ ጽድቅ በሚያሰፍንበት ጊዜ ይፈጸማል።

ሕይወት በዚያን ጊዜ ምንኛ የተለየ ይሆናል! በሰማይ ሆኖ የሚገዛው ኢየሱስ ክርስቶስ “ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፣ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።” አዎን፣ “ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል።”​—⁠መዝሙር 72:13, 14

ሚክያስ 4:4 ስለዚያ ጊዜ ሲናገር “የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፣ የሚያስፈራውም የለም” ብሏል። የአምላክ መንግሥት የሰውን ዘር የሚያሠቃዩትን ችግሮች አልፎ ተርፎም ሕመምና ሞትን ያስወግዳል። አምላክ “ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል።”​—⁠ኢሳይያስ 25:8

እነዚህን ተስፋዎች ያስነገረው አምላክ ራሱ ስለሆነ እንደሚፈጸሙ መተማመን ትችላለህ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ማግኘታቸው የማያጠራጥር መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ለምን አትመረምርም?

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

FAO photo/M. Marzot