ኢሳይያስ 25:1-12
25 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ።
ድንቅ ነገሮችን ስላደረግክና+ከጥንት ዘመን ጀምሮ ያሰብካቸውን ነገሮች*+በታማኝነትና+ እምነት በሚጣልበት መንገድ ስለፈጸምክከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ።
2 ከተማዋን የድንጋይ ቁልል፣የተመሸገችውንም ከተማ የፍርስራሽ ክምር አድርገሃልና።
የባዕዳኑ ማማ፣ ከተማ መሆኑ አብቅቶለታል፤ከተማዋ በምንም ዓይነት ዳግመኛ አትገነባም።
3 ከዚህም የተነሳ ኃያል የሆነ ሕዝብ ያከብርሃል፤የጨቋኝ ብሔራት ከተማም ትፈራሃለች።+
4 ለችግረኛው ምሽግ ሆነሃልና፤ለድሃውም ከደረሰበት ጭንቀት መሸሸጊያ፣+ከውሽንፍርም መጠለያ፣ከፀሐይ ንዳድም ጥላ ሆነሃል።+
የጨቋኞች ቁጣ ከግንብ ጋር እንደሚላተም ውሽንፍር በሚሆንበት ጊዜ ጥበቃ ታደርጋለህ፤
5 ውኃ በተጠማ ምድር እንዳለ ሙቀትየባዕዳንን ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።
በደመና ጥላ እንደሚበርድ ሙቀት፣የጨቋኞችም ዝማሬ ጸጥ ረጭ ይላል።
6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በዚህ ተራራ+ ላይ ለሕዝቦች ሁሉምርጥ ምግቦች* የሚገኙበት ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤+ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ፣መቅኒ የሞላባቸው ምርጥ ምግቦችእንዲሁም የተጣራና ጥሩ የወይን ጠጅ የሚቀርቡበት ታላቅ ግብዣ ያደርጋል።
7 በዚህ ተራራ ላይ ሕዝቦችን ሁሉ የሸፈነውን ከፈንእንዲሁም ብሔራትን ሁሉ ተብትቦ የያዘውን መሸፈኛ ያስወግዳል።*
8 ሞትን ለዘላለም ይውጣል፤*+ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል።*+
በሕዝቡ ላይ የደረሰውን ነቀፋ ከመላው ምድር ያስወግዳል፤ይሖዋ ራሱ ይህን ተናግሯልና።
9 በዚያም ቀን እንዲህ ይላሉ፦
“እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው!+
እሱን ተስፋ አድርገናል፤+እሱም ያድነናል።+
ይሖዋ ይህ ነው!
እሱን ተስፋ አድርገናል።
በእሱ ማዳን ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ።”+
10 የይሖዋ እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋልና፤+ጭድ በፍግ ክምር ላይ እንደሚረገጥሞዓብም በስፍራው እንዲሁ ይረገጣል።+
11 አንድ ዋናተኛ በሚዋኝበት ጊዜ በእጆቹ ውኃውን እንደሚመታእሱም እጁን ዘርግቶ ሞዓብን ይመታዋል፤በእጆቹ በጥበብ በመምታትትዕቢቱን ያበርድለታል።+
12 የተመሸገውን ከተማከረጃጅም የመከላከያ ግንቦችህ ጋር ያፈርሳል፤ምድር ላይ ጥሎ ከአፈር ይደባልቀዋል።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ምክሮች።”
^ ቃል በቃል “ቅባት የሞላባቸው ምግቦች።”
^ ቃል በቃል “ይውጣል።”
^ ወይም “ያስወግዳል።”
^ ወይም “ይጠርጋል።”