ሚክያስ 4:1-13

  • የይሖዋ ተራራ ከፍ ከፍ ይላል (1-5)

    • ሰይፋቸውን ማረሻ ያደርጋሉ (3)

    • ‘በይሖዋ ስም እንሄዳለን’ (5)

  • ዳግመኛ የተቋቋመችው ጽዮን ብርቱ ትሆናለች (6-13)

4  በዘመኑ መጨረሻ*የይሖዋ ቤት ተራራ+ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደዚያ ይጎርፋሉ።+   ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራናወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+ እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።” ሕግ* ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።   እሱ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤+በሩቅ ካሉ ኃያላን ብሔራት ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።* እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+ አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+   እያንዳንዱም ከወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ይቀመጣል፤*+የሚያስፈራቸውም አይኖርም፤+የሠራዊት ጌታ የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።   ሕዝቦች ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው በአምላካቸው ስም ይሄዳሉ፤እኛ ግን በአምላካችን በይሖዋ ስም ለዘላለም እንሄዳለን።+   “በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣“የሚያነክሰውን* እሰበስባለሁ፤ደግሞም የተበተኑትንናያንገላታኋቸውን ሰዎች አንድ ላይ እሰበስባለሁ።+   የሚያነክሰው የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩት* አደርጋለሁ፤+ወደ ሩቅ ስፍራ የተወሰደውንም ኃያል ብሔር አደርገዋለሁ፤+ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበጽዮን ተራራ በእነሱ ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።   አንተም የመንጋው ማማ፣የጽዮን+ ሴት ልጅ ጉብታ ሆይ፣አንተ ወዳለህበት ይመለሳል፤ አዎ፣ የመጀመሪያው* ግዛትህ፣የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለሳል።+   አሁንስ ድምፅሽን ከፍ አድርገሽ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ንጉሥ የለሽም?ወይስ አማካሪሽ ጠፍቷል?ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት የምትሠቃዪው ለዚህ ነው?+ 10  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴትተንፈራገጪ፤ አቃስቺም፤አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትሰፍሪያለሽና። እስከ ባቢሎን ድረስ ትሄጃለሽ፤+በዚያም ይታደግሻል፤+በዚያ ይሖዋ ከጠላቶችሽ እጅ ይዋጅሻል።+ 11  አሁንም ብዙ ብሔራት በአንቺ ላይ ይሰበሰባሉ፤እነሱም ‘የረከሰች ትሁን፤ዓይኖቻችንም ይህ በጽዮን ላይ ሲደርስ ይመልከቱ’ ይላሉ። 12  ይሁንና የይሖዋን ሐሳብ አያውቁም፤ዓላማውንም አይረዱም፤እሱ ገና እንደታጨደ እህል ወደ አውድማ ይሰበስባቸዋልና። 13  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ተነስተሽ እህሉን ውቂ፤+ቀንድሽን ወደ ብረት፣ሰኮናሽንም ወደ መዳብ እለውጣለሁና፤አንቺም ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ።+ በማጭበርበር ያገኙት ትርፍ ለይሖዋ የተወሰነ እንዲሆን፣ሀብታቸውም ለምድር ሁሉ ጌታ ብቻ እንዲውል ታደርጊያለሽ።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በመጨረሻዎቹ ቀኖች።”
ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”
ወይም “ያስተካክላል።”
ወይም “ይኖራል።”
ቃል በቃል “የምታነክሰውን።”
ቃል በቃል “የምታነክሰው ቀሪዎች እንዲኖሯት።”
ወይም “የቀድሞው።”