በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 45

በልቤ የማሰላስለው ነገር

በልቤ የማሰላስለው ነገር

(መዝሙር 19:14)

  1. 1. በልቤ ’ማሰላስለው፣

    ቀኑን ሙሉ የማስበው፣

    አንተን ከልብ ያስደስትህ፤

    ሁሌም ያጽናኝ በመንገድህ።

    ችግር፣ ሐሳብ ሲያስጨንቀኝ፣

    ሌሊት እንቅልፌን ሲነሳኝ፣

    ያኔ ስላንተ ላውጠንጥን፤

    ቀና ሐሳብ እንዲኖረኝ።

  2. 2. ንጹሕ፣ እውነት የሆነውን፣

    በጎ ነገር ያለበትን፣

    ስለ ’ነዚህ ማሰብ ሁሌ፣

    ሰላም ’ሚሰጥ ይሁን ለኔ።

    አንተ ሐሳብህ ድንቅ ነው፤

    ቁጥሩስ ምንኛ ብዙ ነው!

    ይህን አሰላስላለሁ፤

    ትኩረቴም በ’ነዚህ ላይ ነው።

(በተጨማሪም መዝ. 49:3⁠፤ 63:6⁠፤ 139:17, 23⁠ን፣ ፊልጵ. 4:7, 8⁠ን እና 1 ጢሞ. 4:15⁠ን ተመልከት።)