በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 46

ይሖዋ እናመሰግንሃለን

ይሖዋ እናመሰግንሃለን

(1 ተሰሎንቄ 5:18)

  1. 1. ይሖዋ እናመሰግንሃለን፣

    የእውነት ብርሃን ስለበራልን።

    አመስጋኞች ነን ለጸሎት መብታችን፤

    ስለምትሰማ ልመናችንን።

  2. 2. ለውዱ ልጅህ ይድረስህ ምስጋና፤

    በ’ምነት ዓለምን ድል አ’ርጓልና።

    ለምትሰጠን አመራር ተመስገን፤

    ጸንተን እንድንቆም ስለምትረዳን።

  3. 3. አምላክ ሆይ፣ እናመሰግንሃለን፣

    ስለ ክቡር የስብከት ሥራችን።

    በቅርቡ ያልፋል፣ መከራ አይኖርም፤

    ምስጋና ይድረስህ ለዘላለም።

(በተጨማሪም መዝ. 50:14⁠፤ 95:2⁠፤ 147:7⁠ን እና ቆላ. 3:15⁠ን ተመልከት።)