በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 47

በየዕለቱ ወደ ይሖዋ መጸለይ

በየዕለቱ ወደ ይሖዋ መጸለይ

(1 ተሰሎንቄ 5:17)

  1. 1. ወዳምላክ ጸልይ፤ ጸሎት ሰሚ ነው።

    ይሖዋ የሰጠን ታላቅ መብት ነው።

    እንደ ጓደኛህ ሁሉን ንገረው፤

    እምነት የሚጣልበት አምላክ ነው።

    በየ’ለቱ እንጸልይ።

  2. 2. እናመስግነው ሕይወት ሰጥቶናል፤

    ይቅር ባይ ከሆን ይቅር ይለናል።

    ላምላክ ’ንናዘዝ በደላችንን፤

    አፈር እንደሆን ያውቃል ፈጥሮናል።

    በየ’ለቱ እንጸልይ።

  3. 3. በችግር ጊዜ ወደ’ሱ ’ንጸልይ፤

    አባታችን ነው ከኛ ’ማይለይ።

    እንዲጠብቀን እንማጸነው፤

    አይሰጋም የሚታመንበት ሰው።

    በየ’ለቱ እንጸልይ።

(በተጨማሪም መዝ. 65:5⁠ን፣ ማቴ. 6:9-13⁠፤ 26:41⁠ን እና ሉቃስ 18:1⁠ን ተመልከት።)