ለጢሞቴዎስ የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ 4:1-16

  • የአጋንንትን ትምህርት በተመለከተ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (1-5)

  • “የክርስቶስ ኢየሱስ ጥሩ አገልጋይ” (6-10)

    • የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ለአምላክ ማደር (8)

  • ‘ለምታስተምረው ትምህርት ትኩረት ስጥ’ (11-16)

4  ይሁን እንጂ በመንፈስ መሪነት የተነገረው ቃል በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች ከመናፍስት ለሚመነጩ አሳሳች ቃሎችና*+ ለአጋንንት ትምህርቶች ጆሯቸውን በመስጠት ከእምነት መውጣታቸው እንደማይቀር በግልጽ ይናገራል፤  ይህም የሚሆነው በጋለ ብረት የተተኮሰ ያህል ሕሊናቸው የደነዘዘባቸው ግብዝ ሰዎች በሚናገሩት ውሸት የተነሳ ነው።+  እነዚህ ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤+ እንዲሁም እምነት ያላቸውና እውነትን በትክክል የተረዱ ሰዎች ምስጋና አቅርበው እንዲበሏቸው+ አምላክ የፈጠራቸውን ምግቦች+ ‘አትብሉ’ ብለው ያዛሉ።+  ይሁንና አምላክ የፈጠረው ነገር ሁሉ መልካም ነው፤+ በምስጋና እስከተቀበሉት ድረስ ምንም የሚጣል ነገር የለም፤+  በአምላክ ቃልና በጸሎት ተቀድሷልና።  ይህን ምክር ለወንድሞች በመስጠት የእምነትንና አጥብቀህ የተከተልከውን የመልካም ትምህርት ቃል በሚገባ የተመገብክ የክርስቶስ ኢየሱስ ጥሩ አገልጋይ ትሆናለህ።+  ነገር ግን አሮጊቶች እንደሚያወሯቸው ካሉ አምላክን የሚጻረሩ የውሸት ታሪኮች ራቅ።+ ከዚህ ይልቅ ለአምላክ ማደርን ግብ አድርገህ ራስህን አሠልጥን።  የአካል ብቃት እንቅስቃሴ* በጥቂቱ ይጠቅማል፤ ለአምላክ ማደር ግን ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ ሕይወት ተስፋ ስለሚሰጥ ለሁሉም ነገር ይጠቅማል።+  ይህ ቃል እምነት የሚጣልበትና ሙሉ በሙሉ ሊቀበሉት የሚገባ ነው። 10  ጠንክረን በመሥራትና ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ ያለነውም ለዚህ ነው፤+ ምክንያቱም ሁሉንም ዓይነት ሰዎች+ በተለይ ደግሞ ታማኝ የሆኑትን በሚያድነው+ ሕያው አምላክ ላይ ተስፋችንን ጥለናል። 11  እነዚህን ትእዛዛት መስጠትህንና ማስተማርህን ቀጥል። 12  ወጣት በመሆንህ ማንም ሰው ሊንቅህ አይገባም። ከዚህ ይልቅ ታማኞች ለሆኑት በንግግር፣ በምግባር፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርዓያ ሁን። 13  እኔ እስክመጣ ድረስ ለሰዎች ለማንበብ፣+ አጥብቀህ ለመምከርና* ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ። 14  የሽማግሌዎች አካል እጁን በአንተ ላይ በጫነበት+ ጊዜ በትንቢት የተሰጠህን ስጦታ ቸል አትበል። 15  እድገትህ በሁሉም ሰዎች ዘንድ በግልጽ እንዲታይ በእነዚህ ነገሮች ላይ አሰላስል፤* እንዲሁም ትኩረትህ ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ነገሮች ላይ ያረፈ ይሁን። 16  ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ምንጊዜም ትኩረት ስጥ።+ በእነዚህ ነገሮች ጽና፤ ይህን በማድረግ ራስህንም ሆነ የሚሰሙህን ታድናለህና።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ለአሳሳች መናፍስትና።”
እዚህ ላይ የገባው ግሪክኛ ቃል የጅምናስቲክ ስፖርተኛ የሚወስደውን ዓይነት ሥልጠና ያመለክታል።
ወይም “ለማበረታታትና።”
ወይም “አውጠንጥን።”