በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ባለን ረክተን መኖር እንችላለን?

ባለን ረክተን መኖር እንችላለን?

ባለን ረክተን መኖር እንችላለን?

“ረክቶ መኖር ድሃ የሆኑ ሰዎችን ባለጠጋ ያደርጋል፤ አለመርካት ደግሞ ሀብታም የሆኑ ሰዎችን ድሃ ያደርጋል።” —ቤንጃሚን ፍራንክሊን

ዚህ አባባል ጋር በሚስማማ ሁኔታ ብዙ ሰዎች ረክቶ መኖርን እንደ ዕቃ በገንዘብ መግዛት እንደማይቻል ተገንዝበዋል። በመሆኑም ተጨማሪ ንብረት ማፍራትን፣ የተሻለ ስኬት ማግኘትን ወይም ሌሎች የደረሱበት የኑሮ ደረጃ ላይ መድረስን በሚያበረታታው በዚህ ዓለም ውስጥ ሰዎች ባላቸው ነገር ረክተው ወይም ደስተኛ ሆነው መኖር አለመቻላቸው ምንም አያስገርምም! ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ተጽዕኖ አድርገውብህ ያውቃሉ?

ማስታወቂያዎች አንድ ተጨማሪ ነገር ብትገዛ ረክተህ መኖር እንደምትችል የሚገልጹ መልእክቶች ያዥጎደጉዱብሃል።

በሥራ ቦታ ወይም በትምህርት ቤት ያለው የፉክክር መንፈስ፣ ዋጋማነትህ የሚለካው ሌሎች ያከናወኑትን ነገር ማድረግ በመቻልህ ላይ እንደሆነ እንዲሰማህ ያደርግሃል።

ሰዎች ለምታደርግላቸው ነገር አድናቆት የላቸውም።

ጓደኞችህ ባላቸው ነገር ያስቀኑሃል።

ሕይወትን በተመለከተ ለምታነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ አላገኘህም።

እንደነዚህ ያሉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች እያሉም እንኳ ረክተህ መኖር ትችላለህ? ሐዋርያው ጳውሎስ ‘ረክቶ የመኖርን ሚስጥር’ ጠቅሶ ተናግሯል። ብዙ አግኝቶም ሆነ በትንሽ ነገር የኖረባቸው ጊዜያት ነበሩ። ወዳጆቹ ያደንቁት የነበረ ቢሆንም ሌሎች ደግሞ ያፌዙበት ነበር። ሆኖም “በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብሆን ባለኝ ረክቼ መኖርን ተምሬያለሁ” ብሏል።—ፊልጵስዩስ 4:11, 12

ረክቶ ለመኖር የሚያስችሏቸውን እርምጃዎች ወስደው የማያውቁ ሰዎች ረክቶ መኖር የሚለው ሐሳብ ሚስጥር ይሆንባቸዋል፤ ሆኖም ጳውሎስ እንደተናገረው ረክቶ መኖርን መማር ይቻላል። የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትንና ባለን ረክተን ለመኖር የሚረዱንን አምስት ቁልፍ ነገሮች እንድትመረምር እንጋብዝሃለን።